በጋዛ የቆሰሉ ህጻትንና ቤተሰቦቻውን የያዘ የመጀመሪያው አውሮፕላን አረብ ኢሚሬትስ ደረሰ
አረብ ኢምሬትስ የመንግስት ሆስፒታሎች 1 ሺህ ፍልስጤማዊያን ህጻናት እንዲስተናገዱባቸው መወሰኗ ይታወሳል
የአረብ ኢምሬትስ ነብስ አድን ቡድን በግብጽ ራፋ ድንበር በኩል ተጎጂዎችን መቀበል ጀምረዋል
በጋዛ የቆሰሉ 15 ህጻትንና ቤተሰቦቻውን የያዘ የመጀመሪያው አውሮፕላን አረብ ኢሚሬትስ ደረሰ።
ተጎጂዎቹ ወደ አረብ ኢምሬትስ የተጓዙት ሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን የመንግስት ሆስፒታሎች ፍልስጤማዊያን እንዲስተናገዱባቸው ባሳለፉት ውሳኔ መስረት ነው።
- የአረብ ኢሚሬትስ ቆሰሉ ፍሊስጤማውያን ህጻትን ከጋዛ መቀበል ጀመረች
- የአረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት የመንግስት ሆስፒታሎች ፍልስጤማዊያን ህጻናት እንዲጠለሉባቸው ወሰኑ
ተጎጂዎችን ይዞ ከግብጽ አል አሪሽ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው አውሮፕላን አዱድሃቢ መድረሱንም የአረብ ኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በመጀመሪያው ዝር በረራም በጦርነቱ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ እና ቃጠሎ የደረሰባቸው እንዲሁም አስቸኳይ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ህጻናትና ቤተሰቦቻቸው ናቸው ወደ አረብ ኢምሬትስ የተወሰዱት።
ቀሪ ተጎጂዎችን ከጋዛ በማስወጣት ወደ አረብ ኢምሬትስ ለማጓጓዝና አስፈላጊውን ህክምና ለመስጠት የሀገሪቱ የጤና ቡድን አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁም ነው የተገለጸው።
የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ አረብ ኢምሬትስ ለጋዛ ሰርጥ ከተለያዩ ዓለም አቀፍተቋማት በመተባበር አስቸኳይ እርዳታዎችን ስትልክ መቆየቷን የአረብ ኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
አረብ ኢሚሬትስ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር,400 ቶን የምግብ እና የጤና ርዳታ እና የመጠለያ ቁሳቁሶችን የጫኑ 51 አውሮፕላኖች ለጋዛ ልካለች።
በጦርነቱ የቆሰሉ ህጻናትን ከጋዛ የማስወጣት ሂደትም የአረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን የመንግስት ሆስፒታሎች ፍልስጤማዊያን እንዲስተናገዱባቸው ያሳለፉትን ውሳኔ ተከትሎ ነው መተግበር የጀመረው።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት የመንግስት ሆስፒታሎች አንድ ሺህ ፍልስጤማዊያን ህጻናት እና ቤተሰቦቻቸው እንዲስተናገዱባቸው መወሰኗ ይታወሳል።