በፈረንጆቹ 2007 የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩኤኢን ከጎበኙ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ግንኑት ከፍ ብሏል
በፈረንጆቹ 2007 የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩኤኢን ከጎበኙ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ግንኑት ከፍ ብሏል
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (ዩኤኢ) ንጉስ ሸክ ሞሀመድ ቢን ዛይድ አልነሃያንና የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀለቱ ሀገራት በሚኖራቸው የስታራቴጂክ ግንኙነት ተወያይተዋል፡፡
ሽክ መሀመድ ቢን ዛይድ በትዊተር ገጻቸው እንደጻፉት “ከሩሲያው ፕሬዘዳንት ጋር በስልክ አውርቻለሁ…ሁለቱ ሀገራት ሊኖራቸው በሚችለው ስትራቴጂካዊ ግንኙነት፣ሁለቱ ሀገራት ሊተባበሩባቸው በሚችሉባቸው ሌሎች ጉዳዮችና ኮሮናን በመዋጋት ዙሪያ አውርተናል” ብለዋል፡
ኮሮና በሚኖረው ተጽእኖ ላይም እንሰራለን ብለዋል መሀመድ ቢን ዛይድ፡፡ሁለቱ ሀገራት የዲፕማሲ ግንኙነት ከጀመሩ ከፈረንጆቹ 1971 በኋላ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ጉዳዮች ላይ ሲሰሩ ቆይተዋል፤ ሁለቱ ሀጋራት በተለያዩ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ በጋራ እየሰሩ ነው፡፡
በፈረንጆቹ 2007 የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩኤኢን ከጎበኙ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መጠናከሩ ይገለጻል፡፡ የፕሬዘዳንት ፑቲንን ጉብኝት ተከትሎ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናሃያንም በተከታታይ ወደ ሩሲያ ሞስኮ በማቅናት የጎበኙ ሲሆን በተለይ በቅርቡ በፈረንጆቹ 2018 ያደረጉት ጉብኝት የሚታወስ ነው፡፡