ፈረንሳይና ዩኤኢ ግንኙነት የጀመሩት ዩኤኢ ከተመሰረተችበት ከፈረንጆቹ 1971 ጀመሮ ነው
የአቡዳቢ አልጋወራሽና የየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (ዩኤኢ)ምክትል የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሼህ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን ዛሬው እለት በፈረንሳይ ፓሪስ ገብተዋል፡፡
የሞሃመድ ቢን ዛይድ ጉብኝት የሁለቱን መሪዎች የእርስበእርስ ጉብኝት የሚያስቀጥልና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር ተብሏል፡፡
በጋራ ጥቅም ላይ እና በትብብር ላይ የተመሰረተው የፈረንሳይና ዩኤኢ የሁለትዮሽ ግንኙነት የተጀመረው በፈረንጆቹ 1971 ነበር፡፡ ዩኤኢ ከፈረንሳይ ጋር ትብብር ስትመሰርት ሳይንሳዊ ነገሮችን ለማግኘት በማለስም ሲሆን በዚህም ሽብርተኝነትን ፣ጽንፈኝነትንና አጥፊነትን በመዋጋት ከፈረንሳይ ልምድ መቅሰሟ ይነገራል፡፡
የፈረንሳይና የዩኤኢ ግንኙነት፤ ዩኤኢ ከተመሰረተችበት ከፈረንጆቹ 1971 ጀመሮ እምርታ አሳይቷል፡፡