አማካሪው በቀጣይ ኳታርን ጨምሮ አምስት አገራትን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል
የተባበሩት አረብ ኢምሬት የደህንነት አማካሪ ሼክ ታህኑን ቢን ዛይድ ለጉብኝት ኢራን ገብተዋል።
የዩኤኢ የደህንነት አማካሪ ሼክ ታህኑን ቢን ዛይድ አል ናህያን ኢራን ጨምሮ ወደ አምስት አገራት የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ጀምረዋል።
አማካሪው የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ያደረጉት ወደ ኢራን ሲሆን ዛሬ ረፋድ ቴህራን ገብተዋል።
አማካሪው ከኢራን ፕሬዘዳንት ኢብራሂም ሬሲ ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
የደህንነነት አማካሪው በዛሬው የቴህራን ቆይታቸው ከኢራን ብሄራዊ ደህንነት ሃላፊ አሊ ሻምካኒ ጋር ተወያይተዋል።
የደህንነነት አማካሪው ጉብኝት በአካባቢው የተቀዛቀዘውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንደሚያሻሽለው ተገልጿል።
አሊ ሻምካኒ በውይይቱ ላይ እንዳሉት የዩኤኢ የደህንነት አማካሪ ኢራንን መጎብኘታቸው በሁለቱ አገራት እና በአካባቢው አገራት መካከል አዲስ የወዳጅነት መንፈስ እንዲታይ ያደርጋል ብለዋል።
ጉብኝቱ ጥሩ ጉርብትና ከመፍጠሩ ባለፈ በሉአላዊ አገራት የውስጥ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባቶች እንዳይኖሩ እንደሚያደርግም ተገልጿል።
የደህንነነት አማካሪው በቀጣይ ወደ ቱርክ፣ኳታር፣ሳውዲ አረቢያ፣ግብጽ እና ጆርዳን ተጉዘው ከአገራቱ መሪዎች ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
ከአንድ ወር በፊት የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊባግሪ አቡዳቢን የጎበኙ ሲሆን ከዩኤኢ ፕሬዘዳንት የዲፕሎማሲ አማካሪ ጋር በሁለትዮሽ አጀንዳዎች ዙሪያ መምከራቸው ይታወሳል።