ዩኤኢ እጩ አድርጋ ያቀረበቻቸው አል ራዒሲ የኢንተርፖል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ
አዲሱ የኢንተርፖል አለቃ፤ ለባለፉት 3 ዓመታት የኢንተርፖል ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ሲያገለግሉ ቆተዋል
ሜ/ጄ አህመድ ናስር አል ራዒሲ (ዶ/ር) ኢንተርፖልን በፕሬዝዳንትነት ለቀጣዮቹ 4 ዓታት ይመራሉ ተብሏል
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (ዩኤኢ) እጩ አድርጋ ያቀረበቻቸው ሜጀር ጄነራል አህመድ ናስር አል ራዒሲ (ዶ/ር) የዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም (ኢንተርፖል) ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡
ሜ/ጄ አህመድ ናስር አል ራዒሲ ዛሬ በቱርክ አንካራ በተካሄደው የኢንተርፖል ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ሲሆን ለቀጣዮቹ 4 ዓመታት ኢንተርፖልን በፕሬዝዳንትነት ይመራሉ ተብሏል፡፡
አል ራዒሲ በሶስት ዙሮች ከተሰጠው ድምጽ አብላጫውን በማግኘትና የቼክ ሪፐብሊክ ተፎካካሪያቸውን ኮ/ል ሻርካ ሃቭራንኮቫን በመብለጥ ነው የ140 አባል ሀገራትን ድምጽ አግኝተው ያሸነፉት፡፡
ጄነራሉ ዓለም አቀፉን የፖሊስ ተቋም ለመምራት በመመረጤ "ክብር ይሰማኛል" ብለዋል፡፡
ዩኤኢ የ2023ቱ የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ አስተናጋጅ ሆና ተመረጠች
"ኢንተርፖል በአጋርነት ጥንካሬ ላይ የተመሰረተ አስፈላጊ ድርጅት ነው፤ እኔም ለሰዎች እና ለማህበረሰቦች ደህንነቱ የተጠበቀ ዓለም ለመፍጠር በምንሰራበት ጊዜ ይህንን የትብብር መንፈስ የማስቀጥል ይሆናል” ሲሉም ቃል ገብቷል፡፡
አል ራዒሲ ኢንተርፖልን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ለመምራት ወደ ፈረንሳይ ሊዮን እንደሚያቀኑም ነው የተገለጸው፡፡
የኢንተርፖል የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴን የሚቆጣጠሩት ዋና ጸሃፊ ዩርገን ስቶክ በአል ራዒሲ ሹመት መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ዩኤኢ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሆነች
“ኢንተርፖል ተልዕኮውን እንዲወጣ እና የአለም አቀፍ የፖሊስ ትብብርን እንዲደግፍ ለማስቻል ተቀራርበን እንደምንሰራ እጠብቃለሁ”ም ብለዋል ዋና ጸሃፊው፡፡
የፕሬዝዳንት ሼክ ከሊፋ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች አማካሪ ዶ/ር አንዋር ጋርጋሽ በጄነራሉ መመረጥ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
የአል ራዒሲ መመረጥ “በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በህግ ማስከበር መስክ የተገኙ ስኬቶች” ማሳያ እንደሆነም ነው ጋርጋሽ የተናገሩት፡፡
በዩኤኢ የሀገር ውሥጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ዋና ኢንስፔክተር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አዲሱ የኢንተርፖል አለቃ፤ ለባለፉት ሶስት ዓመታትም የኢንተርፖል ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
አል ራዒሲ ኢንተርፖል በፈረንጆቹ 1920 ከተመሰረተ ወዲህ፤ ከመካከለኛው ምስራቅ ተቋሙን ለመምራት የተመረጡ ብቸኛው ሰው ናቸው፡፡
አቡዳቢ፡ በቅርቡ በአለም አቀፍ ደረጃ 286 ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል በኢንተርፖል በሚመራው ከፍተኛ የፀረ-ህገወጥ የሰዎች ማዘዋወር ዘመቻ ከአለም አቀፍ ማዕከላት አንዷ ነበረች።