ዩኤኢ በማደግ ላይ ለሚገኙ ሀገራት የ60 ቢልዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን ገለጸች
የተባበሩተ አረብ ኤምሬትስ (ዩኤኢ) ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ ሀገራቱ ካለቸው የሁለትዮሽ ግንኙነት አንፃር በአብነት የሚነሳ መሆኑን በኢትዮጵያ ዩኤኢ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚና ሚድያ ጉዳዮች ኃላፊ ታላል አል አዚዚ ገለጹ፡፡
ኃላፊው ታላል ኤምባሲው ባዘጋጀው ሴሚናር እንደተናገሩት ከሆነ በዩኤኢ እና ኢትዮጵያ ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እየጎለበተ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
ታላል አል አዚዚ ሁለቱም ሀገራት ያለቸውን ግንኙነት በጊዜ ሂደት እየጎለበተ መጥተዋል እንዲሁም ዩኤኢ እንደ ትምህርት፣ሴቶች ማብቃት፣ጤና፣ኢነርጂ እና የቀይ መስቀል ስራዎች በመሳሰሰሉ ሴክተሮች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር በምሰራት ላይ ነች ብለዋል፡ አሁን በትግራይ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ በማድረግ የበኩልዋን ሚና እየተጫወተች መሆንዋንም ጭምር፡፡
ዩኤኢ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን በመደገፍ እ.ኤ.አ ከ1971 የጀመረ ረዥም ልምድ አላት ያሉት ኃላፊው፤ እስካሁን በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶቿ አማካኝነት 60 ቢልዮን ዶላር ድጋፍ አድርጋለችም ብለዋል፡፡
“የውጭ ግንኙነቷ መሰራታዊ ዓላማ በታዳጊ ሀገራት ያለውን ድህነት ለመቀነስ እንዲሁም ከሀገራት ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጎልበት ነው”ሲሉም ነው ኃላፊው የተናገሩት፡፡
ዩኤኢ በእድገት ላይ ለሚገኙ ሀገራት ከምታደርገው ድጋፍ በዘለለ የተለያዩ የተ.መ.ድ የልማት ድርጅቶች ትደግፋለች እንዲሁም ሰብአዊ እርዳታ ትሰጣለች ያሉት ታላል አል አዚዚ፤ አሁን ላይ የሰብአዊ እርዳታን በማድረግ በመካከለኛው ምስራቅ ቀዳሚ መሆንዋንም አስታውቀዋል፡፡
የኮቪድ-ወረርሺኝ ለመከላከል በተደረገው ርብርብ 1700 ቶን የህክም እና የምግብ እርዳታ ለ128 ሀገራት ድጋፍ ማድረጓን እንደ አብነት ተነስቷል፡፡
የዩኤኢ እና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተለይም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሪፎርም ከመጣበት ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሉ ይታወቃል፡፡