ጎርፍ፣ የበረሃ አንበጣና የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ የሚሹ ሰዎች ቁጥርን ከፍ እንዲል አድርገውታል
ጎርፍ፣ የበረሃ አንበጣና የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ የሚሹ ሰዎች ቁጥርን ከፍ እንዲል አድርገውታል
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (ዩኤኢ) በኢትዮጵያ በጎርፍ ምክንያት ለተፈናቀሉ ሰዎች ምግብ ነክ ድጋፍ አድርጋለች፡፡
በኢትዮጵያ የዩኤኢ ኢምባሲ የባህል ጉዳዮችና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ኃላፊ የሆኑትአሊ አልጋሃፊ በኢትዮጵያ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በጎርፍ የተጎዱትን ሰዎች ለመርዳት ከዩኤኢ ቀይ ጨረቃ የተገኙ ምግብ ነክ የሆኑ እርዳታዎችን በተለይም በአፋር ክልል የለሚገኙ ነዋሪዎች አበርክተዋል፡፡
አሊ አልጋሃፊ እንደገለጹት ዩኤኢ በኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሀ በማጎልበት፣ ትምህርት ቤት በመገንባትና የሴቶችን አቅም በመገንባት መሳተፏን ገልጸዋል፡፡
እርዳታውን የተቀበሉት የኢትዮጵያ የብሄራዊ አደጋ ስጋት አስተዳደር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳመና ዳሮታ በበኩላቸው በጎርፍ ለተፈናቀሉ ሰዎች የዱቄት፣የሩዝና የዘይት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ብለዋል፡፡
ምክትል ኮሚሽነሩ እንደገለጹት በዚህ አመት በኮሮና፣ በበረሃ አንበጣና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈጠረው ድርቅ ፈታኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች 1.44 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ የተፈለገው መጠን አለመገኘቱንና አጋሮችንና ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን የተፈጠረውን የገንዘብ እጥረት እንዲሞሉ ጠይቀዋል፡፡
በዘንድሮ ክረምት በጎርፍ ምክንያት ከ1 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተፈናቅሏል፡፡