የተባበሩት አረብ ኢምሬት ከተመሰረተች ዛሬ 50 ዓመት ሞላት
ለውህደቱ ስኬታማነት ጉልህ ሚናን የተጫወቱት ሼክ ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናህያን የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ነበሩ
የአሁኗ ዩኤኢ ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት ነበር በሰባት ግዛቶች ውህደት የተመሰረተችው
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ከተመሰረተች ዛሬ 50 ዓመት ሞላት፡፡
የመካከለኛው ምስራቅ አገር የተባበሩት አረብ ኢምሬት (ዩኤኢ) በፈረንጆቹ ታህሳስ 2 ቀን 1971 ነበር ዋና ከተማዋን አቡዳቢ በማድረግ በፌዴሬሽን ተዋህዳ የተመሰረተችው፡፡
አገሪቱ የተመሰረተችበትን 50ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር ላይ ትገኛለች፡፡
የአሁኗ ዩኤኢ አቡዳቢ፣ አሻሪቃ፣ራስ አልኽይማ፣ አጅማን፣ ኡም አልቂዊን እና ፉጀይራ የተሰኙ ሰባት ግዛቶችን በማስተባበር አገር ሆናለች፡፡
ዩኤኢ የ 300 ቢሊዮን ድርሃም የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ ይፋ አድርጋለች
የወቅቱ የአቡዳቢ ገዥ የነበሩት ሼክ ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናህያን ሌሎች ስድስት ግዛቶችን በማስተባበር ወደ አገርነት እንድትቀየር በማድረግ ዩኤኢን መስርተው የመጀመሪያው የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሼክ ዛይድ ቢን ሱልጣን አገሪቱን በዓለማችን የቱሪዝም መዳረሻ፣ ነዳጅ ላኪ እና በቴክኖሎጂ የበለጸገች ከማድረግ አንጻር ስኬታማ ስራዎችን በመስራታቸው ዩኤኢ ተጽዕኖ ፈጣሪ አገር እንድትሆን አድርገዋል፡፡
ዩኤኢ የኑክሌር ኃይል ማመንጨት ሥራ መጀመሯን አስታወቀች
በተለይም በአቪዬሽን፣ በዲፕሎማሲ፣ በንግድ፣ በወደብ ልማት፣ በጠፈር ምርምር፣ በቴክኖሎጂ፣ በከባቢ አየር ጥበቃ እና ሌሎችም ጉዳዮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ ተቋማትን መስርተዋል፡፡
በዋናነትም ዩኤኢ ከነዳጅ ጥገኛነት የተላቀቀ ምጣኔ ሃብትን እንድትገነባ መሰረቱ የተጣለው በሼክ ዛይድ ጊዜ ነው፡፡
ዜጎቿ የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲገኙና የተሻለ ኢኮኖሚ እንዲኖራቸው ለማድረግም ሰርተዋል፡፡ በዚህም ዩኤኢ አሁን ላይ ከቀዳሚ የቱሪስት፣ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ስራዎች መዳረሻ ሃገራት አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡
ዩኤኢ የ2023ቱ የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ አስተናጋጅ ሆና ተመረጠች
ዩኤኢ ኑሯቸውንም ሆነ ስራቸውን በሃገሯ ማድረግ ለሚፈልጉ የውጭ ሃገራት ዜጎች የተመቸች ናት፡፡ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከሃገሪቱ ዜጎች የሚልቅ ቁጥር ያላቸው የተለያዩ የውጭ ሃገራት ዜጎች በሃገሪቱ ይኖራሉ፡፡
በመቻቻልና አብሮነት በብዝሃነትም ጭምር ቀድመው ከሚጠቀሱ ሃገራት መካከል ናት ዩኤኢ፡፡
ዜጎቿ እና ወዳጆቿም የተመሰረተችበትን 50 ኛ ዓመት ክብረ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች በማክበር ላይ ይገኛሉ፡፡
ግዙፉ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጎግልም በተለያዩ የፈጠራ መንገዶች ሰንደቅ ዓላማዋን በማውለብለብ መልካም ምኞቱን በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡