አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ለምትገኘው ወሳኝ አጋር የሚደረገው ሽያጭ የአሜሪካን የውጭ ፖሊሲ እና ብሄራዊ ጥቅም የሚያስከብር ነው ብላለች
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር(ፔንታጎን) እንዳስታወቀው ለአረብ ኢምሬትስ የሚሳየል መከላከያ ሲስተም ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት መፈረሙን አስታውቋል፡፡ ፔንታጎን እንደገለጸው ስምምነቱ 2 ነጥብ 25 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ አለው፡፡
የአሜሪካ ውጭ ገዳይ ሚኒስቴር 2 ነጥ 25 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭ አካል የሆነው የታድ ሚሳየል እና የእሳት መቆጣጠሪያ እና የኮሙኒኬሽን ጣቢያ ሽያጨን አጽድቋል፡፡
መግጫው እንደሚለው አረብ ኢምሬት በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ለማስፈን ወሳኝ አጋር ነች፡፡
የአረብ ኢምሬትስ መንግስት ቀደም ብሎ 96 የከፍተኛ ቦታ ሚሳየል መከላከያ ሲስተም ለመግዛት ጠይቆ የነበረ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫ ስምምነቱ የመለዋወጫ፣ የጥገና እና ሲስተሙን ማላመድ ተግባር ያካትታል ብሏል፡፡
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሚለው በመካከለኛው ምስራቅ ለምትገኘው ወሳኝ አጋር የሚደረገው የመሳሪያ ሽያጭ የአሜሪካን የውጭ ፖሊሲ እና ብሄራዊ ጥቅም የሚያስከብር ነው፡፡ አረብ ኢምሬትስ ይህን መሳሪያ መታጠቋ በቀጣይ ያለው የባላስቲክ ሚሳየል ጥቃት ስጋት ይቀርፋል ብሏል፡፡ፔንታጎን እንደሚለው አረብ ኢምሬትስ አሁን ላይ የከፍተኛ ቦታ ሚሳየል ወይም (THAAD) ሲስተምን ስለምትጠቀም መሳሪያዎቹን ከጦሯ ጋር ማዋሃድ እንደማያስቸግራት ገልጿል፡፡