ፖለቲካ
አረብ ኢሚሬትስ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህውሃት ያደረጉትን ስምምነት በበጎ መቀበሏን አስታወቀች
መንግስት ከህወሓት ጋር በዘላቂት ግጭት ለማቆም ተስማምቷል
አረብ ኢምሬትስ ስምምነቱ የኢትዮጵያን ህዝቦች የልማትና የብልጽግና ምኞት የሚያሟላ ነውም ብላለች
አረብ ኢምሬትስ የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሓት ጋር የደረሰውን ስምምነት በበጎ እንደምትቀበለው አስታውቃለች።
አረብ ኤምሬትስ ጥቅምት 23፣2013ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ የተፈረመው ስምምነት የኢትዮጵያን አንድነት የሚያጠናክር መሆኑንም ገልፃለች።
የአረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህውሃት ያደረጉትን የሰላም ስምምነት በበጎ ተቀብሏል።
ሚንስቴሩ በኢትዮጵያ እና በቀጠናው መረጋጋትን የሚያሳድግ ነው ባለው ስምምነት፤ ለስኬቱ አፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ድጋፍ ያደረጉ አካላት፣ ደቡብ አፍሪካንና ኬንያን ገንቢ ሚና ተጫውተዋል ሲል አድንቋል።
የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚንስቴሩ የስምምነቱ ዉሎች የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቶችን ለማመቻቸት አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቅሶ፤ የስምምነቱ ትግበራ ለኢትዮጽያ መረጋጋት እንዲሁም ልማትና ዕድገት እንዲያመጣም ተመኝቷል።
በፌደራል መንግስቱ እና በህወሓት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ሁለት አመት ያስቆጠረውን ጦርነት ይቋጫል ተብሏል።