ውድድሩ በፓሪስ ይደረጋል ተብሏል
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ እንይካሄድ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ወሰነ።
የሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በሩሲያዋ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ግንቦት 28 ቀን 2022 እንዲካሄድ ቀነ ቀጠሮ ቢያዝም በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ቦታው መቀየሩ ተገልጿል።
የ2021/ 2022 የአውሮፓ ሻምፒዮስ ሊግ ሴንት ፔተርስበርግ ከተማ በሚገኘው ጋዝፕሮም አሬና ስታዲየም እንደማይካሄድ አውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ይፋ አድርጓል።
በምትኩም ውድድሩ በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ በሚገኘው ስታዴፍራንስ እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላልፏል።
የሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታን በተመለከተ ማህበሩ ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ነበር። በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ የፍጻሜ ጨዋታው የሚደረግበት ቦታ መቀየሩን ማህበሩ ገልጿል።
በማህበሩ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሴፈሪን የተጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የፍጻሜ ጨዋታውን በታቀደው መሰረት በቅዱስ ፒተርስ በርግ ከተማ ለማካሄድ እንደማይቻል ገምግሞ ቦታውን ቀይሮታል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ውድድሩ በፓሪስ እንዲደረግ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል።
ቀድሞ በወጣ መራሃ ግብር ፒተርስ በርግ በመጪው ግንቦት የሚካሄደውን የሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ጨዋታ እንዲታስተናግድ ብትመረጥም አሁናዊው የዓለም ፖለቲካ የውድድሩን አዘጋጅነት እንዲትቀማ አድርጓታል።