ሊያስቆመን የሚሞክር ማንኛውም አካል በታሪኩ አይቶት የማያውቀው እጣፋንታ ይገጥመዋል-ፑቲን
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች
ፕሬዝዳንት ፑቲን የዩክሬን ወታደሮች መሳሪያቸውን አውርደው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ አሳሰቡ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን በሰጡት አጭር መግለጫ “ሊስቆመን የሚሞክር፣ በሀገራችን እና በህዝባችን ላይ ተጨማሪ አደጋ የሚጥል ማንኛውም አካል በታሪኩ አይቶት የማያውቀው እጣፋንታ ይገጥመዋል” ብለዋል፡፡
የሩሲያ ምላሽ ፈጣን እንደሚሆን የገለጹት ፕሬዝዳንት ፑቲን የወታደራዊ ዘመቻው አላማ በኪቭ አስተዳደር ለበርካታ አመታት ጥቃት እና የዘርማጥፋት ሲፈጸምባቸው የነበሩትን ዜጎች መታደግ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን የዩክሬን ወታደሮች መሳሪያቸውን አውርደው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ አስገንዝበዋል፡፡
የዩክሬን ወታደሮች ትጥቃቸውን የሚፈቱ ከሆነ ከጦርነት ቀጣናው ለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀል እንደሚችሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን አስታውቀዋል፡፡
አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ያሉበት የኔቶ ጦር ወደ ዩክሬን መጠጋቱን ያልወደደችው ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ወታደራዊ ፍጥጫ ውስጥ ገብተው ቆይተዋል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ግዛት ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ተገንጣይ ግዛቶች እውቅና ከሰጠች በኋላ በዩክሬን ላይ ሙሉ ጦርነት ከፍታለች፡፡
ተገንጣይ ግዛቶች ከሩሲያ ወታደራዊ ድጋፍ መጠየቃቸው ሩሲያ ወደ ዩክሬን ግዛት ለመግባቷ አንደኛው ምክንያት ነው፡፡
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬኗ ምስራቅ ዶንባስ ክልል ጦራቸውን በማስማራት ለዩ ወታደራዊ ዘመቻ ማስጀመራቸው ትናት ምሽት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ጦርነቱ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡
ለ30ቀናት የሞቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀችው ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ትናንት ምሽት በሰጡት መግለጫ፤ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦራቸውን ከዩክሬን እንዲያስወጡ ተማጽነዋል
"ፕሬዝዳንት ፑቲን በሰብኣዊነት ስም ጦርህን ወደ ሩሲያ መልስ" ያሉት ጉቴሬዝ፤ ፐሬዚዳንቱ ይህንን ካላደረጉ ውጤቱ በክፍለ ዘመኑ ታይቶ የማይታወቅ ጦርበነት ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው በሩሲያ ቤክሬን ላይ የምትፈጽመውን ወረራ ተከትሎ ለሚደርስ ጥፋት እና ውድመት ዓለም ሩሲያን ተጠያቂ ሊያድርግ ይገባል ብለዋል።