ኡጋንዳ በኮቪድ ምክንያት የተዘጉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቶቿ ለአገልግሎት ክፍት እንምታደርግ አስታወቀች
የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በጥር ወር ለመጀመር ማቀዷንም ፕሬዝዳንቱ ተናግሯል
አስካሁን 122 ሺህ 502 የሚሆኑ ኡጋንዳውያን በኮቪድ-19 እንደተያዙ መረጃዎች ይጠቁማሉ
ኡጋንዳ በኮቪድ ምክንያት የዘጋቻቻው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአገልግሎት ክፍት እንደምታደርግ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዩወሪ ሙሰቪኒ አስታወቁ፡፡
ለአስተማሪዎች፣የትምህርት ተቋማት ሰራተኞች እና ከ18 ዓመት ለሆኑ ተማሪዎች ክትባት መሰጠቱን ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ፤ የተቀሩት የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደፈረንጆቹ በጥር ወር ለመጀመር ታቅዷልም ብሏል፡፡
“ደህንነቱ የተጠበቀ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖርና ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ሁሉም አስተማሪዎች እና ሰራተኞች እንዲከተቡ እጠይቃለው”ም ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት ኮቪድን በማስመልከት በቴሌቭዥ መስኮት ባደረጉት ንግግር፡፡
በሀገሪቱ እንዲከተቡ ከታቀደው 550 ሺህ አስተማሪዎች 269 ሺህ 945 የሚሆኑት የመጀመርያ ክትባት መውሰዳቸው፣ከእነዚህም 96 ሺህ 653 የሚሆኑት ሁለተኛ ዙር ክትባት መውሰዳቸው እንዲሁም 280 ሺህ 055 የሚሆኑት ገና ክትባት ያልወሰዱ መሆናቸውም ተናግሯል ፕሬዝዳንቱ፡፡
ሙሰቪኒ፡ ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱ የሀገሪቱ የትምህርት እና ስፖርት ሚኒስቴር ከርዕሰ መምህራን ጋር በመሆን ክትትል በማድረግ በቫይረሱ የተጠረጠሩ የጤና እክሎች ሲኖሩ ሪፖርት የሚያደርግ ይሆናልም ነው ያሉት፡፡
ኡጋንዳ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ላይ መጨመሩን ተከትሎ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር በሀገሪቱ የሚገኙትን ትምህርት ቤቶች እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መዝጋቷ የሚታወስ ነው፡፡
ቫይረሱ ኡጋንዳ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ 122 ሺህ 502 የሚሆኑ ኡጋንዳውያን በኮቪድ-19 ሲያዙ 3 ሺህ 135 የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው አጥቷል፡፡