ኡጋንዳ እርምጃውን የወሰደችው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በፖለቲካ እንዳይሳተፉ የሚጠይቁ ደንቦችን በመተላፍ ነው ተብሏል
ኡጋንዳ አርብ ዕለት 54 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ ማቋረጧን የገለፀች ሲሆን ከተዘጉት አንደኛው እርምጃውን ፖለቲካዊ ክትትር ነው ብሎታል፡፡
እገዳው በተለያዩ ምክንያቶች የታዘዘ ሲሆን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ሌሎች ቡድኖች በፖለቲካ ውስጥ እንዳይሳተፉ የሚጠይቁ ደንቦችን ባለማክበራቸው መታገዳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በሀገሪቱ ያሉትን በጎ አድራጎት ድርጅቶች በሙሉ የሚመለከተው የመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አካል የቦርድ ብሳቢ ስቲቭ ኦኬሎ “ሥራቸውን አቁመናል” ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል።
እርምጃ የተወሰደባቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በምዕራብ ኡጋንዳ በድፍድፍ ነዳጅ ማምረት ፕሮጀክት የተጎዱትን የፖለቲካ አክቲቪስቶች መብት የሚከላከሉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና የተወሰኑ የመንግስት ባለስልጣናትን አበሳጭቷል፡፡