ፖለቲካ
ኡጋንዳ ከሌባ ላይ ሰርቀዋል የተባሉ 10 ፖሊሶችን በቁጥጥር ስር አዋለች
የኡጋንዳ ፖሊስ በቅርቡ ህገወጥ የሆነ ሰልፍ አካሂደዋል በሚል 11 የምክር ቤት አባላትን አስሮ ነበር
ፖሊሶቹ ከሌቦቹ የያዙትን የገንዘብ መጠን አሳንሰው አቅርበዋል በሚል ነው ተጠርጥረው የተያዙት
ኡጋንዳ ከሌባ ላይ ሰርቀዋል ያለቻቸውን 10 ፖሊሶች በቁጥጥር ማዋሏ ተገልጿል።
የኡጋንዳ ፖሊስ 20 የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎችን አሰረ
የኡጋንዳው ዴይሊ ሞኒተር ጋዜጣ እንደዘገበው ፖሊሶቹ ከሌቦቹ የያዙትን የገንዘብ መጠን አሳንሰው አቅርበዋል በሚል ነው ተጠርጥረው የተያዙት።
መርማሪዎች እንደገለጹት ሶስት ሰዎች ሞተር ሳይክል በመጠቀም ከውጭ ምንዛሬ ቢሮ ሲወጣ ከነበረ ግለሰብ ላይ 110ሺ ዶላር ወይም 407 ሚሊዮን ሽልንግ ሰርቀዋል።
የካምፖላ ፖሊስ፣ 407 ሚሊዮን ሽልንግ በመስረቅ ከተጠረጠሩት ሌቦች ላይ 146 ሚሊዮን ሽልንግ ሰርቀዋል ያላቸውን 10 ፖሊሶች በቁጥጥር ስር አውሏል።
የኡጋንዳ ፖሊስ በቅርቡ ህገወጥ የሆነ ሰልፍ አካሂደዋል በሚል 11 የምክር ቤት አባላትን አስሮ ነበር።
በተወሰኑ የም/ቤቱ አባላት ላይም ጉዳት ደርሶባቸው ነበር።
የምክርቤት አባላቱ በፖሊስ የተያዙት በካምፖላ ከሚገኘው ፖርላማ ዙሪያ ተነስተው ተቃውሟቸውን ወደ ሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ለማሰማት ሲሄዱ በነበረበት ወቅት ነው።