ልዩልዩ
የኡጋንዳ ቤተ ክርስቲያን ለድንግል ሴቶች ዳጎስ ያለ ሽልማት መዘጋጀቱን አስታወቀ
ቤተክርስቲያኑ ድንግል ሴቶችን ለመሸለም ማስታወቂያ ቢያወጣም አሸናፊ አለማግኘቱን ገልጿል
የወንድ ድንግልናን መለየት ባለመቻሉ ለውድድሩ መጋበዝ አልተቻለም ተብሏል
የኡጋንዳ ቤተ ክርስቲያን ለድንግል ሴቶች ዳጎስ ያለ ሽልማት ማዘጋጀቱን አስታወቀ።
የሽልማቱ ዓላማ የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት ለማበረታታት ነው የተባለ ሲሆን፤ ሴቶች ከሰርጋቸው ቀደም ብለው እንዲወዳደሩ ማስታወቂያ አውጥቶ ቆይቷል።
- ከ12 ሚስቶች 102 ልጆችን ያገኙት ኡጋንዳዊ የኑሮ ውድነት ቤተሰቤ እንዳይስፋፋ ገድቦታል አሉ
- የኡጋንዳ ፕሬዝዳት ልጅ ጀነራል ሙሁዚ ኬኒሩጋባ ለአዲሷ የጣሊያን ጠ/ሚኒሰትር የጋብቻ ጥያቄ አቀረቡ
የዚህ ሽልማት አሸናፊ ባሳለፍነው ቅዳሜ መታወቅ ያለበት ቢሆንም ተሸላሚ ድንግል ሴት ማግኘት እንዳልቻለ ቢቢሲ የኡጋንዳ መንግስታዊ ሚዲያ የሆነው ኒው ቪዥንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ቤተ ክርስቲያኗ ባወጣችው ማስታወቂያ እድሜያቸው ለጋብቻ የደረሱ ሴቶች ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት እንዲወዳደሩ ጥሪ አቅርባ ነበር።
የኡጋንዳ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ስቴፈን ካዚምባ፥ ውድድሩ ለሁለቱም ጾታዎች ቢሆንም የወንድ ድንግሎችን መለየት ባለመቻሉ በውድድሩ ማሳተፍ አልተቻለም ብለዋል።
ድንግል የሆኑ ሴቶች ግን በኡጋንዳ እናቶች ህብረት እንዲመዘገቡ ጥሪ የተደረገ ሲሆን፥ ከተመዘገቡ በኋላ አሸናፊዎቹ ይለያሉ ተብሎም ነበር።
ይሁንና ለውድድሩ አሸናፊ ድንግሎች ዳጎስ ያለ የገንዘብ ሽልማት ብናዘጋጅም አሸናፊ አላገኘንም ብለዋል ሊቀ ጳጳስ ካዚምባ።
ይሁንና ሊቀ ጳጳሱ ለውድድሩ አሸናፊ ድንግሎች ስለሚሸለመው ገንዘብ መጠን ከመናገር ተቆጥበዋል።