ኡጋንዳዊው ቸብቸጋይ በሞናኮ የ5ኪሜ ሩጫ ውድድር ሪከርድ ሰበረ
ኡጋንዳዊው ቸብቸጋይ በሞናኮ የ5ኪሜ ሩጫ ውድድር ሪከርድ ሰበረ
ኡጋንዳዊው አትሌት ጆሹዋ ቸብቸጋይ በሞናኮ በተካሄደው የ5ኪሜ ሩጫ ወድድር በ12 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ በመጨረስ ሪከርድ መስበር ችሏል፡፡
የ10ሺ ኪሜ የአለም ሻምፒዮና አሸናፊው በጥሩ ሁኔታ በመሮጥ ኬንያዊው ኪፕሩቶ በቫሌንሺያ በ13 ደቂቃ ከ18 ሰከንድ የፈጀ ጊዜ በመሮጥ ያስመዘገበውን ምርጥ ሰአት አሻሽሎታል፡፡
ባለፈው ዓመት ኳታር ዶሀ በተካሄደው የአለም ሻምፒዮና ውድድር ቸብቸጋይ ወርቅ በማምጣት ሲያሸንፍ፣ ኬንያዊው ኪፕሩቶ ደግሞ የብር ሜዳሊያ በማምጣት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቆ ነበር፡፡