ፖለቲካ
የብሪታንያ መሳሪያ አምራች ለዩክሬን መሳሪያ ለማቅረብ በኪየቭ ቢሮ ከፈተ
ቢኤኢ ዩናይትድ ኪንግደምና ሌሎች ሀገራት ለዩክሬን ያልኳቸው አብዛኞቹን መሳሪያዎች አምርቷል
ዩናይትድ ኪንግደም የኪየቭ ከፍተኛ መሳሪያ አቅራቢ ሀገር ናት
የዩናይትድ ኪንግደም ታዋቂ የመከላከያ ኩባንያ ቢኤኢ ለዩክሬን መሳሪያና ትጥቅ ለማቅረቅ ስምምነት ፈርሟል።
ኩባንያው በዩክሬን ህጋዊ እንቅስቃሴ ለማድረግም በኪየቭ ቢሮ ከፍቷል።
ድርጅቱ እርምጃው አጋሮችን ለማግኘት በቀጥታ መስራትን እንደሚፈቅድለት ገልጾ፤ ቀላል መሳሪያዎችን በኪየቭ ለማምረትም አይኑን ጥሏል።
ቢኤኢ ዩናይትድ ኪንግደምና ሌሎች ሀገራት ለዩክሬን ያላኳቸው አብዛኞቹን መሳሪያዎች ማምረቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
የሩሲያ-ዩክሬን ከተጀመረ ከየካቲት 2022 ጀምሮ ዩናይትድ ኪንግደም የኪየቭ ከፍተኛ መሳሪያ አቅራቢ ሆናለች።
የዩክሬይን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሀገራቸው ውስጥ የጦር መሳሪያ ማምረቻ መክፈት ቅድሚያ የሚሰጠው ልማት መሆኑን በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ላይ አስፍረዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት ከኩባንያው ስራ አስፈጻሚ ቻርለስ ውድበርን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው።
ኪየቭ የጦር መሳሪያና የለሎች የመከላከያ ትጥቅ አቅርቦትን ለማሳደግ ልዩ ፍላጎት አላት።
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከጀመረ ወዲህ የአክሲዮን ድርሻው በ75 በመቶው ያሻቀበው ቢኤኢ፤ ለዩክሬን ጦር ስልጠናና የጥገና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።