የብሪታንያ ኩባንያዎች ሳምንታዊ የስራ ቀናትን ወደ አራት ቀናት ዝቅ አደረጉ
በአውሮፓ የሳምንታዊ የስራ ቀናትን ከአምስት ወደ አራት ቀናት ዝቅ በማድረግ ላይ ናቸው
ኩባንያዎች ሰራተኞቻቸው አራት ቀናትን እንዲሰሩ እና የአምስት ቀናት ክፍያ መክፈል አዋጭ ሆኗል ብለዋል
የብሪታንያ ኩባንያዎች ሳምንታዊ የስራ ቀናትን ወደ አራት ቀናት ዝቅ አደረጉ፡፡
በአብዛኛው የአለማችን ክፍል በሳምንት ውስጥ አምስት ቀናትን በስራ ማሳለፍ መደበኛ ያደረጉ ሲሆን ይህ አሰራር እየተቀየረ መጥቷል፡፡
ሰራተኞች በስራቸው ደስታ ማጣት፣ አረፍት አልባ ህይወት ማሳለፍ እና ስራቸውን መጥላት ተቋማትን ውጤታማ አለማድረጉን በየጊዜው የወጡ ጥናቶች አሳይተዋል፡፡
ብሪታንያ ላለፉት ስድስት ወራት በሙከራ ደረጃ ስትተገብረው የነበረውን የአራት ቀናት ስራ ፕሮግራም ውጤታማ ሆኖልኛል ብላለች፡፡
በዚህም ምክንያት የብሪታንያ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሳምንታዊ መደበኛ የስራ ቀናትን ከአምስት ቀናት ወደ አራት ቀናት ቀይረዋል፡፡
አዲሱ አሰራር ሰራተኞች በሳምንት አራት ቀናት ስራ እንዲሰሩ ነገር ግን የአምስት ቀናት ደመወዝ እንዲከፈላቸው የሚያደርግ ነው፡፡
ሰራተኞች በሳምንት ውስጥ አራት ቀናትን ብቻ ሲሰሩ ስራቸውን የሚወዱ፣ ደስተኛ እና ፍሬያማ ሆነዋል ተብሏል፡፡
በወር 500 ዩሮ እና በላይ ደመወዝ ይጨመርልን ያሉ የሉፍታንዛ አየር መንገድ ሰራተኞች ስራ አቆሙ
ይህ አሰራር ውጤታማ መሆኑን ተከትሎ ስኮትላንድ ከግል ተቋማት በተጨማሪ በተመረጡ የመንግስት ተቋማት መተግበር ጀምራለች ሲል ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
በአውሮፓ ሳምንታዊ የስራ ቀናትን ወደ አራት ቀናት የማሳጠር እቅድ በስፋት በመተግበር ላይ ሲሆን ቤልጂየም እና ጀርመን ዋነኞች ሆነዋል፡፡
ቤልጂየም ከሙከራ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ሳምንታዊ የስራ ቀናትን ወደ አራት ቀናት የቀየረች ሲሆን ጀርመን ገና በሙከራ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
ይሁንና መንግስታት አዲሱን የስራ ቀናት መተግበር እንዳልጀመሩ ሲገለጽ በቀጣይ ፓርቲዎች ዋነኛ የምረጡኝ ቅስቀሳ አጀንዳ ሊያደርጉት እና ሊተገብሩት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡