የወሲብ ቪዲዮዎችን በስልካቸው መመልከታቸውን ያመኑት የብሪታኒያ ፓርላማ አባል ከስልጣን ታገዱ
ከፓርላማ አባልነታቸው የተጋዱት ነይል ፓሪሽ “አዎ በእብደት ጊዜ ሁለቴ “የወሲብ ቪዲዮዎችን ተመልክቻለሁ” ሲሉ ጥፋታቸው አምኗል
ነይል ፓሪሽ፤ ከዚህ በኋላ የፓርላማ አባል ሆኖ መቀጠሉ ፋይዳ የለውም ብሏል
የወሲብ ቪዲዮዎች ወይም ፖርኖግራፊ በስልካቸው መመልከታቸው ያመኑት የብሪታኒያ ፓርላማ (ሃውስ ኦፍ ኮሞንስ) አባል መታገዳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከፓርላማ የታገዱት ግለሰብ በጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ወግ አጥባቂ ፓርቲ የሚመራውን የወግ አጥባቂዎቹ ፓርቲ (ኮንሰርቫቲቭ) አባል መሆናቸውም ተግልጿል፡፡
ነይል ፓሪሽ ሊጋለጡ የቻሉት ሁለት ሴት የፓርላማ አባላት “ፓሪሽ የወሲብ ቪዲዮዎችን እንደሚመለከቱ” ለፓርላማ ኮሚሽነር ሪፖርት ማድረጋቸው ተከትሎ ነው፡፡
ከፓርላማ አባልነታቸው የተጋዱት ነይል ፓሪሽ በበኩላቸው “አዎ በእብደት ጊዜ ሁለቴ ወሲብ ቀስቃሸ ምስሎች ተመልክቻለሁ” ሲሉ አምኗል፡፡
በዚህም ፓሪሽ ጥፋታቸውን ለፓርላመው ኮሚሽነር ማሳወቃቸውን ተከትሎ፤ የወግ አጥባቂዎቹ ፓርቲ ከስልጣን አግዷቸዋል፡፡
ባለፈው ቅዳሜ ስራቸውን የለቀቁት ፓሪሽ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ መልኩ ምርመራ ሲደረግ፤ በፓርላማ አባልነታቸው እንደሚቀጥሉ ተናግረው የነበረ ቢሆኑም፤ ከአሁን በኋላ በአባልነት ለመቀጠል እንደሚቸገሩ አስታውቋል፡፡
በዚህም ፓሪሽ "በመጨረሻም በቤተሰቤ እና በምርጫ አካባቢ ላይ እየፈጠረ ያለውን ንዴት እና ጉዳቱ ስመለከት መቀጠሉ ፋይዳ እንዳልነበረው አይቻለሁ" ሲሉም እንባ እየተናነቃቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
የደቡብ ብሪታኒያዎቹ ቲቨርተን እና ሆኒተን የምርጫ ክልሎችን የወከሉት የ65ቱ ዓመቱ ፓሪሽ ለ12 ዓመታት በፓርላማ አባልነት ያገለገሉ ናቸው፡፡
የቲቨርተን እና ሆኒተን የምርጫ ክልሎች ቃል አቀባይ፤ የወግ አጥባቂዎቹ ፓርቲ ፓሪሽ ለሰጡን አገልግሎት ያመሰግናል ብሏል፡፡
"ከፓርላማ አባልነት ለመልቀቅ የወሰኑት ውሳኔ እንደግፋልን" ም ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፡፡
ፈገግ የሚያሰኘው ደግሞ አንድ ፓሪሽ የተባሉት አርሶ አደር ተመሳሳይ ስም ያለው ድረ-ገጽ ላይ ትራክተሮች ሲፈልጉ በአጋጣሚ አንድ ምስል ተመለልተው ሲያበቁ “ላደርገው የማይገባኝን ትንሽ ተመልክቻለሁ” የሚል አስተያየት ማስፈራቸው ነው፡፡