በፈረንጆች 2022/23 በደመወዝ ገምጋሚ አካል አቅራቢነት የሰጠውን ጭማሪ ዳግም እንደማያስተካክል ገልጿል
የእንግሊዝ ነርሶች የስራ ማቆም አድማ መቱ
የደከማቸውን እና ወጪያቸውን ለመሸፈን እየታገሉ ያሉት የእንግሊዝ ነርሶች የስራ ማቆም አድማ ጀምረዋል።
በእንግሊዝ ውስጥ በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ ነርሶች ረቡዕ እለት ከሆስፒታሎች በመውጣት የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል።
ወጪያቸውን ለመሸፈን መቸገራቸውና የስራ ጫና ብዙዎችን ወደ ውሳኔው ገፋፍቷቸዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የእንግሊዝ ነርሶች እንደ አምቡላንስ ሠራተኞች፣ ባቡር አሽከርካሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ የፖስታ ቤት ሠራተኞች እና በሌሎች በርካታ ዘርፎች ያሉ ሰራተኞች የዋጋ ግሽበት በ10 በመቶ ሲጨምር የተሻለ ክፍያ እና ሁኔታዎችን በመፈለግ እርምጃ እየወሰዱ ነው።
አድማው በነርሶች ማህበር በሮያል የነርስ ኮሌጅ ከተደረጉት በደርዘን የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፎች አንዱ ነው የተባለ ሲሆን፤ በ100 ዓመት ታሪኩ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በጅምላ የወጣው የኢንዱስትሪ እርምጃው ሁለተኛ ማዕበል ነው ተብሏል።
መንግስት በፈረንጆች 2022/23 በደመወዝ ገምጋሚ አካል አቅራቢነት የሰጠውን ከአራት እሰከ አምስት በመቶ ጭማሪ ዳግም እንደማያስተካክል በመግለጽ የነርሶችን የደመወዝ ውይይት ፍላጎት ለማሟላት እስካሁን እየተደረገ ያለውን ጫና ተቋቁሟል።
የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ስቲቭ ባርክሌይ ረቡዕ እለት ወደ ሆስፒታል በሄዱበት ወቅት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በአድማው መከፋታቸውን ገልጸው፤ የነርሶችን የደመወዝ ጥያቄዎች ማሟላት የማይቻል ነው ብለዋል ።