ሶስት የአውሮፓ ሀገራት ከሩሲያ የሚመጣን ስጋት ለመቋቋም ትብብር መፈጸማቸውን ገለጹ
ሩሲያ በግዛቷ ውስጥ ጦሯን በየትኛውም ቦታ ማንቀሳቀስ መብቷ መሆኑን እየገለጸች ነው፡፡
አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር በዝግጅት ላይ ሲሉ አስጠንቅቀዋል
ብሪቴን፣ፖላንድና ዩክሬን ከሩሲያ ሊመጣ የሚችለውን ወታደራዊ ጣልቃገብነት ለመቀልበስ በማሰብ ትብብራቸውን ለማጠናከር እየሰሩ መሆናቸውን የሶስቱ ሀገራት መሪዎች በኪቭ ተናግረዋል፡፡
የሶስቱ ሀገራት ትብብር የቀድሞዋን የሶቬት ህብረት ግዛት ዩክሬንን በሩሲያ ወደሚጠላው የወታደራዊ ጥምረት ኔቶ እንደሚያቀርባት ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ሩሲያ በዩክሬን ድንበር በ100ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን እያስጠጋች መሆኑን እና ይህንም ምእራባውያን እደሚቃወሙት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡
ሩሲያ ግን ዩክሬንን የመወረር ፍላጎት እንደሌላት እና አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ጦራቸውን ወደ ቀድሞ የሶቬት ህብረት አባል ሀገራት አንዳያስገቡ ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡
ሩሲያ በግዛቷ ውስጥ ጦሯን በየትኛውም ቦታ ማንቀሳቀስ መብቷ መሆኑን እየገለጸች ነው፡፡
የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትር ዴኒስ ሽሚጋል በቅርቡ ዩክሬን-ፖላንድ-ዩኬ የተባለ ቀጣናዊ ጥምረት በማቋቋም በሩሲያ የተደቀነው ወረራ እና ቀጣናዊ ደህንነት እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል፡፡
የፓላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞራዊኪ በበኩላቸው ፖላንድ የጋዝ እና የመሳሪያ ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ የዩክሬን አካል የነበረችውን ክሪሚያ ግዛትን በኃይል ከያዘች በኋላ በሩሲያ በምእራባውያን ሀገራት መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡
አሜሪካና አጋሮቿ አሁን ላይ ሩሲያ በዩክሬን ድንበር በምታደርገው ወታደራዊ ዝግጅት ለቁስለኞች የሚሆን ደም ማካተቷን እና የሩሲያ የወረራ እቅድ አይቀሬ መሆኑን የሚያሣይ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡