በዩኬ የፍይዘርና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው አስትራዜናካ ክትባቶች እስካሁን ጥቅም ላይ ውለዋል
በዓለም ከፍተኛ የኮሮና ተጠቂና ሞት ያስመዘገበችው ዩናይትድ ኪንግደም(ዩኬ) የኮሮና ቫይረስን ያያችበት መንገድ በሰፊው አስተችቷት ነበር፡፡ ነገርግን ክትባት የማደረስ ስራው የተለየ መልክ እንዳለው ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ክትባቱ ከጸደቀ 10 ሳምንታት በኋላ የዩኬ መንግስት ክትባቱ ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው 15 ሚሊዮን ሰዎች በማዳረስ አላማውን አሳክቷል፡፡ የፒፋይዘር ባዮቴክ ክትባት ከጸደቀ ከቀናት በኋላ ክትባቱ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በብሪስቶል የሚገኘውን አሽተን ጌት ስቴዲየም ተገኝተው የክትባቱን ሁኔታ አይተዋል፡፡ በሳምንት ሰባት ቀናትና በቀን ለ12 ሰአታት ክፍት የሆነው በሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ስቴዲየሙ እየገቡ ይገኛሉ፡፡
የጥንቃቄና ደህንነት ኃላፊ የሆኑት ዴቭ ስቶር “ይህ በእውነት በቱቦ ቀዳዳ ጫፍ የታየ መብራት ነው ብለዋል፡፡”“ሁላችን ከዚህ በተቻለ ፍጥነት መውጣት እንፈልጋለን፡፡ ሁሉም የራሱን ድርሻ መወጣት አለበት፤እኛም ጥሩ ነገር እየሰራን ነው፡፡ የሚያስፈልገው ይሄ ነው፤ መተባበርና የጤና ባለሙያዎች ስራቸውን እንዲሰሩ ማድረግ፡፡”
ቫይረሱ መጀመሪያ በተከሰተበት ወቅት ዩኬ ባልተመረመሩ ክትባቶች ላይ ብዙ ገንዘብ አፍስሳ ነበር፡፡ ሀገሪቱ በፍጥነት መንቀሳቀስ ምናልባት እንዱ ፍቱን ይሆናል በሚል ሃሳብ ብዙ ገንዘብ አውጥታለች፤ ብዙ ትእዛዝም ከተለያዩ ኩባንያዎች አዝዛ ነበር፡፡
የፍይዘር ባዮቴክና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው አስትራዜናካ ክትባቶች እስካሁን ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ የሞደርና ክትባት ደግሞ እንደደረሰ ጥቅም ላይ ይውላል፤ ሌሎችም ቀጥለው ይመጣሉ ተብሏል፡፡ በዩኬ በሆስፒታሎችና ቁልፍ በሆኑ ትልልቅ ቦታዎች ሲሰጥ የነበረው ክትባት አሁን በፍጥነት ወደ ብዙ የክትባት ቦታዎች ተስፋፍቷል፡፡ አሁን ላይ 1500 በላይ የክትባት ማእከላት አሉ፡፡