ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ኮለኔል ገነራል ኦሌክሳንደር ሲርስኪ የዩክሬን ጦር አዛዥ አድርገው ሾመዋል
ዩክሬን ተወዳጁን የጦር አዛዥ ለምን ከሀላፊነት አነሳች?
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የጀመረችው ጦርነት ሶስተኛ ዓመቱን ሊያከብር ጥቂት ቀናት ብቻ በቀረበት ወቅት የጦር አዛዧን ከሀላፊነት አንስታለች፡፡
ባለ አራት ኮከቡ ጀነራል ቫለሪይ ዛሉኒ ባለፉት ዓመታት ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ስታደርገው የነበረውን ጦርነት ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ከቀርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ጋር አለመግባባት መከሰቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
አሜሪካ በዩክሬን ጉዳይ የአቋም ለውጥ ማድረጓ ተገለጸ
ዩክሬናዊያን ከፕሬዝዳንቱ ይልቅ በጀነራል ቫለሪ ላይ የበለጠ ዕምነት ነበራቸው የተባለ ሲሆን ይህም ላለመግባባቱ ዋነኛ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀርም ተገልጿል፡፡
የዩክሬን ወታደሮች በየጦር ግንባሩ “ጌታ እና ጀነራል ቫለሪ ከእኛ ጋር ካሉ ድሉ የእኛ ነው” የሚል መፈክር ያሰሙ ነበርም ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ሹም ሽሩን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ጀነራል ዛለሪ ዛሉዝኒ የዩክሬን ቀጣይ ውጊያ እቅድ የለውም፣ ሊያቀርብልኝም አልቻለም ማለታቸውን ዎልስትሪት ጆርናል ዘግቧል፡፡
ያሉ ሲሆን በዚህ ምክንያት ላለፉት አራት ዓመታት የምድር ጦር አዛዥ የነበሩት ኮለኔል ጀነራል ኦሌክሳንደር ሲርስኪን የሀገሪቱ ጦር አዛዥ አድርገው ሾመዋል፡፡
በሩሲያ ጦር አካዳሚ እንደተማሩ የሚታወቁት ኮለኔል ጀነራል ኦሌክሳንደር ጨካኝ ናቸው በሚል የሚታወቁ ሲሆን በተለይም በውጊያ ለሚሞቱ ወታደሮች ነፍስ ሀዘኔታ እና ርህራሄ የላቸውም በሚል ይታወቃሉ ተብሏል፡፡
ከሀላፊነት የተነሱት ጀነራል ዛሉዝኒ በዩክሬናዊያን ተወዳጅ መሆናቸውን ተከትሎ ወደ ፖለቲካ ሊገቡ እንደሚችሉ ቢነገርም ጀነራሉ እስካሁን ስለ ቀጣይ እቅዳቸው ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡
ዝምተኛው ጀነራል ዛሉዝኒ ዩክሬን በሩሲያ የተወሰደባትን ግዛቶች ለማስመለስ ብርቱ ጥረት አድርገዋል ቢባልም ከካርኪቭ ውጪ ሌሎቹን ማስመለስ እንዳልቻሉ እና ዩክሬን ሩሲያን ለማሸነፍ የቴክኖሎጂ የበላይነት መውሰድ እንዳለባት መናገራቸው ይታወሳል፡፡