የዩክሬን መንግስት ሀገሪቱ ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ጦርነት በበላይነት የሚመሩትን ከፍተኛ የጦር አዛዥ የማባረር እቅድ እንዳላት ለአሜሪካ ተናግሯል
ዩክሬን ከፍተኛ የጦር አዛዧን ለማባረር እቅድ እንዳላት ገለጸች።
የዩክሬን መንግስት ሀገሪቱ ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ጦርነት በበላይነት የሚመሩትን ከፍተኛ የጦር አዛዥ የማባረር እቅድ እንዳላት ለአሜሪካ መናገሯን ሮይተርስ ዘግቧል።
ከፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የተጋጩትን ጀነራል ቫለሪ ዛሉዝኒን የማባረረ እቅድ፣ ዩክሬን ባለፈው አመት ያወጀችው የመልሶ ማጥቃት እና በሩሲያ የተያዙ ቦታዎችን የማስመለስ እቅድ አለመሳካቱን ተከትሎ የመጣ ነው።
ሮይተርስ ለፕሬዝደንት ዘለንስኪ ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ጠቅሶ እደዘገበው ጀነራሉ ግማሽ ሚሊዮን ጦር እንዲመለመል ባቀረቡት ሀሳብ ላይ አልተግባቡም።
ነገርግን ዘገባው ጨምሮ እንደገለጸው ሁኔታዎች እስከሚስተካከሉ የዩክሬን ጦር አዛዥ የሆኑትን ጀነራል ዛሉዝኒን የመተካት ሂደት ለጊዜው ቆሟል።
እንደዘገባው ከሆነ አሜሪካ በጀነራሉ የማባረር እቅድ ላይ አቋሟን አልገለጸችም።አሜሪካ በዚህ ጉዳይ ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ እንደሌላት አሳውቃለች ተብሏል።
ሮይተርስ አዲስ ወታደሮች በመመልመል እቅድ ጉዳይ በፕሬዝደንቱ እና በጀነራሉ መካከል ልዩነት የተፈጠረው፣ ፕሬዝደንቱ አሁን ያለው የሰው ኃይል በቂ ነው በማለታቸው ነው።
"ዛሉዝኒ ግማሽ ሚሊዮን ወታደሮች መመልመል አስፈላጊ ነው ይላሉ። ዘለንስኪ አሁን አስፈላጊ አይደለም" ማለታቸው አለመግበባት መፈጠሩን ዘገባው ጠቅሷል።
ዛሉዝኒ ሀገሪቱ በቂ ወታደር መመልመል አልቻለችም የሚል ይዘት ያለው ጽሁፍ በሲኤንኤን ላይ አስፍረዋል።
"ብረቱ ጀነራል" በመባል የሚታወቁት ጀነራል ዛሉዝኒ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያላቸው ናቸው።
የዛሉዝኒ ከስልጣን መነሳት 1000 ኪሎሜትር በሚረዝም ግንባር ከፍተኝ የተተኳሽ ክምችት ያላትን የሩሲያን ግዙፍ ኃይል የመከቱትን የዩክሬን ወታደሮች ሞራል ሊጎዳ ይችላል ተብሏል።