የዩክሬን-ሩሲይል ጦርነት ሁለት ዓመት ሊሞላው ሁለት ወራት ብቻ ቀርተውታል
ዩክሬን በየዕለቱ 800 ወታደሮቿ እያጣች እንደሆነ ተገለጸ።
ለሁለት ሳምንት በሚል በልዩ ዘመቻ የተጀመረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት 20 ዉር ሞልቶታል።
ጦርነቱ እንዲቆም ከማዕቀብ ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም አሁንም ውጊያው መበርታቱ ተገልጿል።
የቀድሞው የጀርመን አየር ሀይል አባል እና ወታደራዊ ጉዳዮች ተንታኙ ኮለኔል ራልፍ ቴሌ እንዳሉት ዩክሬን በየዕለቱ 800 ወታደሮቿን በሞት እና አካል ጉዳት ምክንያት እያጣች ነው ብለዋል።
እንደ ተንታኙ ገለጻ ዩክሬን እየደረሰባት ያለውን የወታደሮች ሞት ለማካካስ በየወሩ 20 ሺህ አዲስ ሰራዊት መመልመል ይጠበቅባታል።
የአውሮፓ ፖለቲካ እና ወታደራዊ ማህበረሰብ መሪ የሆኑት ቴሊ የዩክሬን ወታደሮች ያላቸው የመዋጋት ፍላጎት መቀዛቀዙን ገልጸው በአንጻሩ እየተዋጉ ያሉት ከፍተኛ የመዋጋት ስነ ልቦና ካለው የሩሲያ ጦር ጋር መሆኑ ጉዳቱን እንዳባባሰውም ተናግረዋል።
ዩክሬን ከዚህ በተጨማሪም የጦር መሳሪያዎቿ እየተመናመኑ መሆኑን፣ ከኔቶ አባል ሀገራትም የሚለገሱ መሳሪያዎች ተዓምር የሚያመጡ አይደሉም ሲሉም ተንታኙ አክለዋል።
ተንታኙ አክለውም ሩሲያ በዚህ ጦርነት ያጣችው የሰው ሀይል እና የጦር መሳሪያ ቀላል እንዳልሆነ ጠቅሰዋል።
በቀጣይ ጊዜያት ሩሲያ በጦርነቱ የበላይነት መያዟ አይቀሬ ነው ያሉት ተንታኙ ይህም ዩክሬን ተጨማሪ ግዛቶቿን ልትነጠቅ እንደምትችልም ተናግረዋል ሲል ፎከዝ መጋዚን ዘግቧል ።
የሩሲያ መከላከያ ሚንስትር ሰርጊ ሼጉ ከዚህ በፊት በሰጡት መግለጫ ጦርነቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ 400 ሺህ የዩክሬን ወታደሮች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ተናግረው ብለው ነበር።