ሩሲያ በዶኔትስክ ክልል የሚገኙ ከተሞችን ለመያዝ ባክሙትን እንደ መወጣጫ እየተጠቀመች ነው ተብሏል
ዩክሬን ባክሙት በዋግነር ቅጥር ወታደሮች መያዙን ውድቅ አደረገች
ለወራት ሞስኮ ምስራቃዊ ዩክሬንን አቋርጣ ለማለፍ ስልታዊ የሆነችውን ባክሙት ለመያዝ እየገሰገስኩ ነው ብላለች።
የዩክሬን እና ሩሲያ ኃይሎች ከተማዋን እንደሚቆጣጠሩ እየዛቱ ነው።
የዩክሬን ጦር ከ20 በመቶ በላይ ከተማዋን ተቆጣጥሬያለሁ ብሏል።
ባክሙት ለሩሲያ እና ዩክሬን ለምን አስፈላጊ ሆነች
የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደር ዋግነር ቡድን ከ80 በመቶ በላይ ባክሙትን ይዣለሁ ማለቱ ከእውነት የራቀ ነውም ብሏል።
የሩሲያ መከላከያ ሚንስቴር የዋግነር ጦር ሦስት የከተማዋን ክፍሎች መያዙን ገልጾ፤ የሩስያ ኃይሎች የዩክሬን ጦር ሰብሮ ለመግባት ሲሞክር መደምሰሳቸውን ተናግሯል።
ሞስኮ "ልዩ ወታደራዊ ተልዕኮ" ብላ በጠራችው ጦርነት በዋናነት ባክሙትን በመያዝ በዶኔትስክ ክልል የሚገኙ ከተሞችን ለመያዝ እንደ መወጣጫ ድንጋይ አድርጋ ታያታለች።
የዩክሬን ምስራቃዊ ወታደራዊ እዝ ቃል አቀባይ ሰርሂ ቼሬቫቲ ዋግነር ቡድን ከተማዋን 80 በመቶ ይዣለሁ ማለቱን ለሮይተርስ በሰጡት አስተያየት ውድቅ አድርገዋል።
"በእርግጠኝነት መናገር የምችለው የዩክሬን የመከላከያ ኃይሎች የባክሙትን ግዛት በጣም ትልቅ በሆነ መጠን እንደተቆጣጠሉ ነው" ብለዋል።
ዋግነር እንዳስታወቀው ኃይሎቹ የአስተዳደር ማዕከሉን፣ ፋብሪካዎችን፣ መጋዘኖችን እና የማዘጋጃ ቤት ህንጻዎችን ጨምሮ አብዛኛውን ባክሙትን ተቆጣጥሯል።