ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለዩክሬን ሽንፈት ተጠያቂው መላው ዓለም ነው አሉ
ሩሲያ በምስራቃዊ ዩክሬን በኩል በሩሲያ የበላይነት የተወሰደብኝ ዓለም የጦር መሳሪያ ስላላቀረበ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል
ፕሬዝዳንቱ ካርኪቭን ለሩሲያ መስጠት በጭራሽ የማይታሰብ መሆኑን ጠቅሰዋል
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ለዩክሬን ሽንፈት ተጠያቂው መላው ዓለም ነው አሉ፡፡
የዓለምን ምግብ እና ነዳጅ እንዲጨምር ያደረገው የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት አሁንም መቋጫ ያላገኘ ሲሆን ጦርነቱ በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ ቀጥሏል፡፡
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰሜናዊ ዩክሬን በኩል የሩሲያ ግስጋሴን ማቆም ያልቻለችው ዩክሬን በርካታ መንደሮችን ተነጥቃለች፡፡
የሩሲያ ግስጋሴ ካርኪቭ የተሰኘችውን የዩክሬን ሁለተኛዋ ትልቋ ከተማን ለመቆጣጠር ዓላማ ያደረገ ሲሆን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ወደ ጦር ግንባር ሄደው ወታደሮቻቸውን አነቃቅተዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በውጊያ ለቆሰሉ የዩክሬን ወታደሮች ተኝተው በሚታከሙበት አልጋ በመሄድ ሜዳሊያ ሸልመዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላ ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት ለዩክሬን ሽንፈት ተጠያቂው መላው ዓለም ነው፣ የጦር መሳሪያዎችን ቶሎ ቢያደርሱን ኖሮ ወታደሮቻችን ከጦር ሜዳ አያፈገፍጉም ነበር ብለዋል፡፡
በካርኪቭ በኩል ያለው ውጊያ እጅግ ከባድ እና ልዩ ትኩረትን የሚጠይቅ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ወደ ስፔን እና ፖርቹጋል ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ለመሰረዝ መገደዳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ካርኪቭን ማጣት አንችልም፣ የጦር መሳሪያ ድጋፎቹ መዘግየታቸው በጦር ግንባር ላይ ትልቅ አስተዋጽኦም ነበራቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የጦር መሳሪያ እርዳታዎቹ በመዘግየታቸው በሰሜን ምስራቃዊ ዩክሬን በኩል ባሉ ውጊያዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩክሬን ተዋጊዎች ህይወታቸውን አጥተዋል የተባለ ሲሆን
የሩሲያ ጦር በሰሜን ምስራቅ ዩክሬን የሚገኙ 5 መንደሮቸን ተቆጣጠረ
ለጦር መሳሪያ እርዳታው መዘግየት ተጠያቂዋ አሜሪካ ናት በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም በፍጹም ፑቲን ተጨማሪ የዩክሬን ይዞታዎችን እንዲቆጣጠር እድሉን ሰጥተውታል ይህ ደግሞ የአሜሪካ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ስህተት ነው ብለዋል፡፡
አሜሪካ ከአንድ ወር በፊት 60 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን እንደምትሰጥ የገለጸች ሲሆን አሁን ደግሞ ተጨማሪ 2 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አሳውቃለች፡፡