የዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭ በደረሰባት አየር ድብደባ ከባድ ፍንድታ እንደተሰማ የከተማዋ ከንቲባ ተናገሩ
ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭ ላይ ከባድ የአየር ድብደባ አደረሰች።
በደረሰው የአየር ድብደባ ከባድ ፍንድታ እንደተሰማ የከተማዋ ከንቲባ ቪታሊ ክሊስችኮ ተናገሩ።
በድብደባው የደረሰው ጉዳት እስካሁን አልታወቀም።
ይህ ድብደባ ከመስከረም መጨረሻ ወዲህ የመጀመሪያው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
"በከተማ የግራ ጫፍ በኩል ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰምቷል"ሲሉ ክሊስችኮ በቴሌግራም ገጻቸው ጽፈዋል።
ፍንዳታው ከመሰመታቱ ከደቂቃዎች በፊት የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደውሎች ተሰምተው ነበር።
የከተማ ባለስልጣናትም የከተማዋ ነዋሪዎች አደጋ እንዳይደርስባቸው ወደ መጠለያ እንዲገቡ ሲያስጠነቅቁ ተደምጠዋል።
አሜሪካን ጨምሮ በምዕራባውያን ሀገራት በምትደገፈው ዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ያለው ጦርነት አንዴ ሞቅ፣ እንዴ ቀዝቀዝ እያለ ቀጥሏል።
ሩሲያ ልዩ ባለችው ወታደራዊ ዘመቻ አወዛጋቢ የሆነ ህዝበ ውሳኔ በማድረግ አራት የዩክሬን ግዛቶችን ወደራሷ ጠቅልላለች።
ሁለቱን ሀገራት ለማስማማት የተደረገ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ውጤት አላመጡም።