ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ካወጀች በኋላ ብዙም ሳይቆይ ነበር የችቺኑ መሪ ሩሲያን በመደገፍ ጦር ማዝመቱን የገለጸው
የችቺኑ መሪ ራምዛን ካዲሮቭ በዩክሬን ላይ ዝቷል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ካወጀች በኋላ ብዙም ሳይቆይ ነበር የችቺኑ መሪ ሩሲያን በመደገፍ ጦር ማዝመቱን የገለጸው።
ካድሮቭ አሁንም በዩክሬን ያሉ ናዚዎችን እናጸዳለን የሚል ማስፈራሪያ በማሰማት ለሩሲያ እና ለፕሬዝደንት ፑቲን ያለውን አጋርነት አሳይቷል።
ካድሮቭ በሩሲያ ሰራሽ ቱ-72 ታንክ ላይ ሆኖ "ጠብቁን፤ ኪቭ ገብተን ናዚን እናጸዳለን" ሲል ዝቷል።
የሩሲያ ታንኮች የምዕራባውያን የሚበልጡ ናቸው ሲል ካድሮቭ ተናግሯል።
የችቺኑ መሪ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር ያለው ቀረቤታ የአባት እና የልጅ አይነት ነው እየተባ ይነገራል።
የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ካድሮቭ ሶስት ልጆቹን ለውጊያ የመላክ ፍላጎት እንዳለው መግለጹ ይታወሳል።
ካዲሮቭ ይህን ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ በሩሲያ ጦር ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ የደረጃ እድገት ተሰጥቶታል፤ ካድሮቭም በእድገቱ ትልቅ ኩራት እንደተሰማው ሲገልጽ ነበር
የችቺን ወታደሮች ከመደበኛው የሩሲያ ጦር ጋር በዩክሬን እየተዋጉ ናቸው።