ዩክሬን በዛፖሮዥያ በኩል ያለውን የሩሲያ የመከላከያ መስመር ሰበርኩ አለች
የሩሲያ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ሃና ማሊያር የኪቭ ወታደሮች ብዙ በተወራለት የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ በዛፖሬዥያ ግዛት በኩል ቦታ ማስለቀቃቸውን ተናግረዋል
ዩክሬን በትናንትናው እለት እንደገለጸችው ወታደሮቿ በበርካታ ቦታዎች ያሉ የሩሲያን መከላከያ መስመሮች መጣሳቸውን ገልጻች
ዩክሬን በዛፖሮዥያ ግዛች የተዘረጋውን የሩሲያ መከላከያ መስመር መስበሯን አስታውቃለች።
ዩክሬን በትናንትናው እለት እንደገለጸችው ወታደሮቿ በበርካታ ቦታዎች ያሉ የሩሲያን መከላከያ መስመሮች መጣሳቸውን ገልጻች።ምንምእንኳን ወታደሮቹ የመጀመሪመያ የሆኑትን የሩሲያ ምሽጎች መስበር ቢችሉም አሁንም ጠንካራ የሆነ የሩሲያ ምሽግ ከፊታቸው አጋጥሟቸዋል ብላለች።
የሩሲያ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ሃና ማሊያር የኪቭ ወታደሮች ብዙ በተወራለት የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ በዛፖሬዥያ ግዛት በኩል ቦታ ማስለቀቃቸውን ተናግረዋል።
አሜሪካም ባለፈው አርብ እንደገለጸችው የኪቭ ወታደሮች ባለፉት 72 ሰአታት በደቡብ ግንባር የሚታይ ለውጥ አምጥተዋል ብላለች።
"በብዙ ቦታዎች እና አቅጣጫዎች ጥቃት አለ። እና በተወሰኑ ቦታዎች የመጀመሪያው መከላከያ ምሽግ ተሰብሯል" ብለዋል ማሊየር።
ማሊየር አክለውም በከፍተኛ ሁኔታ በፈንጅ በታጠረውን አካባቢ ለማለፍ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት የኪቭ ወታደሮች አሁን ላይ ወደ ዋናዎቹ የሩሲያ ምሽጎች ላይ ደርሰዋል ብለዋል።
በምዕራባውያን በምትታገዘው ዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ያለው ጦርነት ቀጥሏል፤ ግጭቱን በድርድር ለመፍታት የተደረጉ ሙከራዎች ውጤት አልባ ሆነዋል።