የሩሲያ ባለስልጣናት ጥቃቱን ዩክሬን አደረሰችው ብለዋል
የሩሲያ ባለስልጣናት ዩክሬን ያደረሰችው ነው ያሉት የድሮን ጥቃት በስድስት ግዛቶች መድረሱን ተናግረዋል።
ጥቃቱ ጦርነቱ ከተጀመረ ከ18 ወራት ወዲህ የተፈጸመ ትልቁ ነው ተብሏል።
ሩሲያ ከእስቶኒያና ላቲቪያ ጋር በምትዋሰንበት በምዕራብ ፔስኮፍ ግዛት አየር ማረፊያን ድሮን የደበደበ ሲሆን፤ በጥቃቱ እሳት መፈጠሩ ተነግሯል።
በዚህ ጥቃቱ አራት አውሮፕላኖች ጉዳት እንደደረሰባቸው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተናግረዋል።
የግዛቱ አስተዳዳሪ በጥቃቱ ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለመመርመር በረራዎችን መሰረዛቸውን አስታውቀዋል።
በማህበራዊ የትስስር ገጾች የተለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እሳት እና ጭስ አሳይተዋል። የአካባቢው አስተዳደር በጥቃቱ የሞተ ሰው እንደሌለና እሳቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል።
ፔስኮቭ በድሮን ጥቃቱ ጉዳት የደረሰበት ብቸኛው ግዛት መሆኑ ተነግሯል።
አንዳንድ መገናኛ ብዙኸን ከ10 እስከ 20 የሚሆኑ ድሮኖች ግዛቱን ሳያጠቁ አልቀረም ብሏል።
የሩሲያ መከላከያ ሚንስቴር የድሮን ጥቃቱ በሞስኮ ዙሪያ ጨምሮ በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች መፈጸሙን ገልጿል።
ሆኖም ድሮኖቹ ተመተው እንዲወድቁ መደረጉን ሚንስቴሩ ጠቅሶ፤ ጉዳትና ሞት አልደረሰም ብሏል።