ዩክሬን አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ መተኮሷን ተከትሎ ምን አዳዲስ ነገሮች ተከስተዋል?
ዩክሬን ከአሜሪካ የተላከላትን የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ ግዛት ለመጀመሪያ ጊዜ ተኩሳለች
ሩሲያ ድርጊቱ ምእራባውያን የከፈቱባት አዲስ የጦርነት ምዕራፍ መሆኑን በመግለጽ ተመጣጣኝ ርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች
ዩክሬን ከአሜሪካ የተላከላትን የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ ግዛት ለመጀመሪያ ጊዜ መተኮሷን ተከትሎ አዲስ ውጥረት ነግሷል።
ዩክሬን ከአሜሪካ በተላኩላትን የአርሚ ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም (ATACMS) ሚሳኤሎች ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሩሲያ ግዛት በመተኮስ ጥቃት መፈጸሟን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር ጋር ግንኙን ያለው የቴሌግም ገጽ ዩክሬን ከአሜሪካ የተሰጣትን የአርሚ ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም (ATACMS) ሚሳኤሎችን ትክክለኛው ስፍራ ካልተገለጸበት የየከሬን ግዛት ውስጥ ሲተኮስ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት በበኩላቸው፤ ዩክሬን ካሏት የአርሚ ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም (ATACMS) ሚሳኤሎች ውስጥ ስምቱን ወደ ሩሲያ መተኮሷን እና ከእነዚህም ውስጥ ሁለቱን ሩሲያ አየር ላይ ማምከኗን አስታውቋል።
ሚሳዔሎቹ በሩሲያዋ ባርያንስክ ክልል ውስጥ የምትገኘ እና የ18 ሺህ ሰዎች መኖሪያ በሆነችው ክራቼቭ ከተማ የሚገኝ የጥይት ማከፋፈያ መምታቸውን ባለስጣናቱ አስውቀው፤ ነገር ግን የጉዳቱ መጠን አሁንም ጥናት ይፈልጋል ብለዋል።
የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ከተተኮሱበት ሚሳዔሎች ውስጥ አምስቱ ተመትተው አየር ላይ ሲከሽፉ አንደኛው ግን ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል።
የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ጥቃቱ ማክሰኞ ጧት በሰሜን ዩክሬን በሚያዋስነው ብራያንስክ ክልል ላይ ያነጣጠረ መሆኑን አረጋግጧል።
አዳሩን ሁለቱም ሀገራት ማለትም ሩሲያ እና ዩክሬን አዳሩን እርስ በራሳቸው መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት መፈጸማቸው ተነግሯል።
በኪየቭ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው እለት ሩሲያ ከፍተኛ የአየር ጥቃት ልታደርስ መሆኑን መረጃ እንደደረሰው በመግለጽ ኤምባሲውን ለጊዜው ዘግቷል።
ሩሲያ ዩክሬን በአሜሪካ ሰራሽ የአርሚ ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም (ATACMS) ሚሳኤሎች ለፈጸመችው ጥቃት ተመጣጣኝ አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።
ድርጊቱ ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ የጀመሩት አዲስ የጦርነት ምዕራፍ መሆኑንና ለዚህም በየደረጃው ተመጣጣኝ ርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቃለች።
የሩሲያው ፕሬዝዳንቱ ቭላድሚር ፑቲን በትናትው እለት የተሻሻለውንና የሩሲያን የኒዩክሌር መሳሪያ አጠቃቀም የሚወስነው ህግ ማጽደቃቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።
በብርያንስክ ክልል የሚገኝ የሩሲያን ወታደራዊ ጣቢያ መቷል የተባለውና እስከ 300 ኪሎሜትሮች የሚጓዘው የአሜሪካ ሚሳኤል (ATACMS) የዋሽንግተን እና ሞስኮን ፍጥጫ አባብሷል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ዋሽንግተን የኒዩክሌር ጦርነት ከሚያስነሳ ተግባሯ እንድትታቀብ ማሳሰባቸውን ክሬምሊን ጠቁሟል።
ሩሲያ በ2020 በይፋ ያወጣችውን የኒዩክሌር ህግ ማሻሻሏን ስትገልጽ የቆየች ሲሆን፥ ባይደን ለኬቭ ይሁንታ በሰጡ ማግስት ነው ፑቲን ማሻሻያውን ያፀደቁት።
ማሻሻያው ኒዩክሌር ያልታጠቁ ሀገራት ከታጠቁት ጋር በመተባበር በሩሲያ ላይ ጥቃት ካደረሱ በሞስኮ ላይ “የጋራ ጥቃት” እንደከፈቱ ይቆጠራል የሚል ሃሳብ አካቷል።
ሩሲያ የኒዩክሌር መሳሪያዎቿን መቼ መጠቀም እንዳለባት በግልጽ የሰፈረበት ህግ፥ ድንበር አቋራጭ የሚሳኤል፣ የአየር እና ድሮን ጥቃት ከተፈጸመባት አውዳሚዎቹን መሳሪያዎች መጠቀም እንደምትጀምር የሚፈቅድ ነው።