አምባሳደር ፕሪስቴይኮ "ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከእንቅልፋቸው እንደተነሱ ብሪታንያን ያመሰግናሉ" ሲሉ ትችት ሰንዝረዋል ተብሏል
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ በብሪታንያ የዩክሬን አምባሳደርን ከስራ አገዱ።
ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ በብሪታንያ የዩክሬን አምባሳደር የነበሩት ቫዲም ፕሪስቴይኮ ከሰሞኑ በሀገራቸው ፕሬዝዳንት ላይ ትችትን ሰንዝረዋል በሚል ከስራ ታግደዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ አውሮፓዊያን ለዩክሬን እየሰጡት ያለው የጦር መሳሪያ እንደዘገየባቸው እና እርዳታውም በቂ እንዳልሆነ ተናግረው ነበር።
- ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ዩክሬንን እንዲጎበኙ ጋበዙ
- የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የሶስተኛው የዓለም ጦርነት ፍርሃት 'ምክንያታዊ' ነው አሉ
ብሪታንያን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ንግግር ቅር መሰኘታቸውን በተለያየ መንገድ ገልጸዋል።
የብሪታንያ መከላከያ ቤን ዋላስ እንዳሉት ዩክሬን ለተደረገላት ድጋፍ ምስጋና ልታቀርብ ሲገባ ወቀሳ ውስጥ ገብታለች፣ የኪሽን ምስጋና ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም ብለዋል።
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ በበኩላቸው ዩክሬን ለተደረገላት ድጋፍ ዋጋ ልትሰጥ ይገባል ብለዋል።
የቤን ዋላስን ንግግር ተከትሎም ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ "ሚንስትሩ እንዴት ማመስገን እንዳለብኝ ሊነግረኝ ይፈልጋል" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
በብሪታንያ የዩክሬን አምባሳደር ቫዲም ፕሪስቴይኮ በትዊተር ገጻቸው ላይ የፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ንግግር የጤና አይደለም ሲሉ ተሳልቀዋል ተብሏል።