ሶልንሴፕዮክ የተባለ የመረጃ ጠላፊዎች ቡድን የዩክሬን ግዙፍ የሞባይ ተቋም ላይ የሳይበር ጥቃት ፈጽሟል
የእስኤልና የፍልስጤሙ ሃማስ ወደ ጦርነት ማምራታቸውን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ወራት የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ትኩረት ተነፍጎት ቆይቷል።
ዓለም ትኩረቱን መካከለኛው ምስራቅ ላይ ቢያደርግም በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በምስራቅ ዩክሬን እና በሌሎች አካባቢዎች ተባበሶ መቀጠሉ ተነግሯል።
ጦርነት
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ዛሬ 659ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፤ ጦርነቱ አሁንም ኪቭን ጨምሮ በተለያዩ ግንባሮች መቀጠሉ ተነግሯል።
ሩሲያ በትናንትናው እለት በኪቭ የሚሳዔል ጥቃት የሰነዘረች ሰንዝራለች፤ በጥቃቱም ቢያስ 53 ዩክሬናውያን ሞተዋል የተባለ ሲሆን፤ ስድስት ህጻትን ጨምሮ 18 ሰዎች ቆስለዋል።
ሩሲያ በኪቭ ከተማ ላይ በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሳዔል ጥቃት የሰነዘረች ሲሆን፤ የከተማዋ የአየር መቃወሚያ አብዛኞቹን ማውደሙን አስታውቋል።
የዩክሬን የአየር መከላከያ ስርዓት ኢስካንዴር ኤም እና ኤስ 400 የተባሉ ሚሳዔሎችን መትቶ መጣሉን መትቶ ጥሏል የተባለ ሲሆን፤ ሆኖም ግን ሚሳዔሎቹ ሲወድቁ ጉዳት አድርሰዋል ነው የተባለው።
ዩክሬን አሁን የመጀረውን በረዶዋማ ጊዜ ተከትሎ ከሩሲያ ለሚጠብቃት ከባድ ውጊያ አዳዲስ ምልምል ወታደሮችን በፖላንድ እያሰለጠነች ነው።
በበረዶ በተሸፈኑ ምሽጎች በአስቸጋሪ ሁኔታ እየተደረገ በሚገኘው ልምምድ የፖላንድ፣ ፈረንሳይና ቤልጂየም ወታደሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
የዩክሬን ምልምል ወታደሮች ስልጠናቸውን እንዳጠናቀቁ በቀጥታ ወደ ግንባር ተመድበው ከሩሲያ ጋር ይፋለማሉ ተብሏል። ኬቭ በሰኔ ወር ጀመረችው የተባለው የመልሶ ማጥቃት እስካሁን የረባ ውጤት እንዳላስገኘ ተገልጿል።
በሌላ ዜና ግዙፉ የዩክሬን የሞባይስል ስልክ ኔትዎርክ ላይ በተፈጸመ የሳይበር ጥቃት በሚሊየን የሚቆጠሩ ዩክሬናውያንን ከስለክ ግንኝነት ጋር አቆራርጧል።
ሶልንሴፕዮክ የተባለ የመረጃ ጠላፊዎች ቡድን ኪቭስታር በተባለ ግዙፉ የዩክሬን የሞባይስል ስልክ ኔትዎርክ ላይለተፈጸመው የሳይበር ጥቃት ኃፊነት ወስዷል።
የሳይበር ጥቃቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የስልክ አገልግሎትና የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ እንዳይደርሳቸው ማደረጉ የተነገ ሲሆን፤ ዩክሬን ሳይበር ጥቃቱን የፈጸመው ቡድን ከሩሲያ ጦር ደህንነት ጋር ግንኙነት አለው ብላለች።
ፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ
ከአውሮፓ ህብረት መሪዎች በዩክሬን አባልነት ጉዳይ ላይ የሚደረግ ድርድር በይፋ እንዲጀመር ለመወሰን ዛሬ ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሏል።
ከአሜሪካ ጉብኝት ወደ አውሮፓ ከተመለሱ በኋላ በኖርዌይ ጉብኝት ያደረጉት የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የኪየቭን ከአውሮፕ ህብረት አባልነት የሚያግድበት ምንም ምክንያት የለውም ብለዋል።
ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ እና አይስላንድ በበኩላቸው የፈለገውን ጌዜ ቢፈጅም ከዩክሬን ጎን እንደሚቆሙ ለፕሬዝዳንት ዘዜለንስኪ ቃል ገብተዋል።
አምስቱ ሀገራት የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ እንስቶ እስካሁን 11 ቢሊየን ዩሮ ለዩክሬን ድጋፍ አድርገዋል።