ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነች-ፑቲን
ሩሲያ በአለም አቀፍ ደረጃ የዩክሬን ነው ተብሎ እውቅና ከተሰጠው ግዛት ውስጥ 17.5 በመቶን ተቆጣጥራለች
ምዕራባውያን ባለስልጣናት ፑቲን ትክክለኛ ንግግር ለማድረግ የአሜሪካን ምርጫ እየጠበቁ ናቸው ቢሉም፣ በፑቲን በተደጋጋሚ ለንግግር ዝግጁ መሆናቸው ገልጸዋል
ሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
ሞስኮ የራሷን ብሔራዊ ጥቅም እንደምትጠብቅ የገለጹት ፑቲን ሩሲያ የሚፈልጉ ከሆነ ከዩክሬን፣ ከአሜሪካ እና ከአውሮፖ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነች ብለዋል።
ምዕራባውያን ባለስልጣናት ፑቲን ትክክለኛ የንግግር ጥረት ለማድረግ የአሜሪካን ምርጫ እየጠበቁ ናቸው ቢሉም፣ በፈረንጆቹ 2022 በዩክሬን ላይ ጦር ያዘመቱት ፑቲን በተደጋጋሚ ለንግግር ዝግጁ መሆናቸው ገልጸዋል።
ፑቲን "በዩክሬን ውስጥ በሩሲያ ላይ የተናደዱ፣በአውሮፖ እና በአሜሪካ ያሉ መደራደር ይፈልጋሉ? እሽ ካሉ ይሁን። ነገረግን ብሔራዊ ጥቅማችንን በሚያስከብር መልኩ እንነጋገራለን"ብለዋል።
"የራሳችን የሆነን ነገር አንሰጥም"።
ሩሲያ በአለም አቀፍ ደረጃ የዩክሬን ነው ተብሎ እውቅና ከተሰጠው ግዛት ውስጥ 17.5 በመቶን ተቆጣጥራለች።
በ2014 ክሬሚያን የተቆጣጠረችው ሩሲያ ባለፈው አመት በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈተች በኋላ በከፊል የተቆጣጠረቻቸውን አራት ግዛቶች ወደ ግዛቷ አጠቃላለች።
ፑቲን የዩክሬን የኔቶ አባልት ተቀባይነት እንደማይኖረው ተናግረዋል።
በገንዘብ እና በጦር መሳሪያ በምዕራባውያን የምትደግፈው ዩክሬን በሩሲያ የተያዙ ግዛቶቿን ለማስለቀቅ፣ ሩሲያ ደግሞ አራቱን ግዛቶች ሙሉ ለሙሉ ለመያዝ ጦርነቱን ቀጥለዋል።