ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት በአብዛኛው ግንባር ላይ ድሮኖችን በብዛት እየተጠቀመች ነው
ዩክሬን በየወሩ 10 ሺህ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖች (ድሮኖች) እየወደሙባት መሆኑን አዲስ የወጣ ሪፖርት አመላከተ።
የብሪታኒያ ወታደራዊ ቲንክታንክ ተቋመወ ባወጣው ሪፖርት፤ ዩክሬን በሩሲያ እያደረች ባለው ጦርነት ለማመን አዳጋች በሆነ መለኩ 10 ሺህ ድሮኖችን እያጣች ነው ብሏል።
የዩክሬን ድሮኖች ከጥቅም ውጪ እየሆኑ ያሉት በሩሲያ ኤሌክሮኒክ ጠለፋ ምክያት መሆኑንም ተቋሙ በሪፖርቱ አመላክቷል።
ሪፖርቱ የዩክሬን ወታደራዊ አመራርን እና ሶስት ማንነታቸው ያልተጠቀሱ ምንጮችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ በተሰራ መሆኑን ኒውዮርክ ታይም ዘግቧል።
ወደ ሁለተኛ ዓመቱ እየተጠጋ ባለው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ላይ ዩሲያ የጦር ታክቲኮችን ጨምሮ አስገራሚ ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎችን እና የጦር መሳሪያዎችን እየተጠቀመች ቢሆንም፤ በኤሌክትሮኒካዊ ጦርነት ላይ ያለው ክፍል ትኩረትን የሚስብ ነው ተብሏል።
የኤሌክትሮኒክ ጦርነት የሩስያ የትግል መንገድ ወሳኝ አካል ሆኖ መቀጠሉ የተገለፀ ሲሆን፤ ሩሪያ በየ 10 ኪሎ ሜትር የጦር ግንባር ክልል ውስጥ አንድ የኤሌክትሮኒክ የጦር ስርዓት ትጠቀማለች፤ ይህም ድሮኖችን ለመከላከል ነው ተብሏል።
የሩሲያ ጦር በጦርነቱ ስፍራ ላይ የኤሌክትሮኒክ የጦር ስርዓት በስፋት መጠቀሙን ቀጥሏልያለው ሪፖርቱ፤ ይህም ዩክሬን ላይ ከፍተኛ የድሮን ኪሳራ እያደረሰ መሆኑንም ሪፖርቱ አመላክቷል።