የዩክሬን ፖርላማ የውትድርና መመልመያ እድሜን ዝቅ ለማድረግ ረቂቅ ህግ አቀረበ
ይህ ረቂቅ ህግ ይፋ የተደረገው ዩክሬን ከሩሲያ እያደረገች ያለው 22 ወራትን ያስቆጠረው ጦርነት በሚፈለገው ደረጃ አለመሄዱን ተከትሎ ነው
በትናንትናው እለት ሩሲያ በዶኔስክ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ ያለችውን ማሪንካ ከተማ መሉ በመሉ መቆጣጠሯን አስታውቃልች
የዩክሬን ፖርላማ የውትድርና መመልመያ እድሜን ዝቅ ለማድረግ ረቂቅ ህግ አቀረበ።
በዩክሬን ፖርላማ ዌብሳይት ላይ ፖስት የተደረገው ረቂቅ ህግ ለውጊያ የሚመለመሉ ወታደሮችን እድሜ መነሻ ከ27 ወደ 25 ዝቅ እንዲል ሀሳብ አቅርቧል።
ይህ ረቂቅ ህግ ይፋ የተደረገው ዩክሬን ከሩሲያ እያደረገች ያለው 22 ወራትን ያስቆጠረው ጦርነት በሚፈለገው ደረጃ አለመሄዱን ተከትሎ ነው።
ባለፈው እሁድ ዩክሬን የሩሲያን ወታደራዊ ጀቶች መትታ መጣሏን ገልጻ ነበር። ነገርግን ሩሲያ እንዳልተመቱባት አስተባተበለች።
በትናንትናው እለት ሩሲያ በዶኔስክ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ ያለችውን ማሪንካ ከተማ መሉ በመሉ መቆጣጠሯን አስታውቃልች።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሾይጉ ከፕሬዝደንት ፑቲን ጋር ባደረጉት ስብሰባ "ጦራችን በዛሬው እለት ማሪንካን መሉ በመሉ ነጻ አድርጓል"ብለዋል።
ፑቲን ከዶኔስክ ከተማ በደቡም ምዕራብ በኩሉ በአምስት ኪሎሜትር ላይ የምትገኘውን ከተማ መቆጣጠር፣ ለሩሲያ ኃይሎች የጠላትን ጦር ከዶኔስክ ለማራቅ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።
ነገርግን የዩክሬን ጦር ቃል አቀባይ ኦሌክሳንደር ሽቱፑን ከተማዋን ላለማስደፈር ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው ሲሉ ለዩክሬን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ "ወታደሮቻችን በማሪንካ ከተማ አስተዳደር ድንበር ላይ ናቸው፤ ከተማዋን ለመከላከል ውጊያው ቀጥሏል"ብለዋል።
ሞስኮ ከተማዋን መያዟ እውነት ከሆነ ከባለፈው ግንቦት ወዲህ ለሩሲያ ትልቅ ስኬት ነው ተብሏል።
22 ወራትን ባስቆጠረው የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት እጅግ ደም አፋሳሽ በተባለው ጦርነት ሩሲያ ባለፈው ግንቦት ወር ባክሙት ከተማን መቆጣጠር ችላለች።
ረቂቅ ህጉ የትኞቹ የዩክሬን ዜጎች እንደሚመለመሉ እና የመመልመያ እድሜ መነሻውን ወደ 25 ዝቅ ማለቱን ይገልጻል።
በመከላከያ ሚኒስትሩ ሩስቴም ኡመሮቭ የተፈረው አጭር ማብራሪያ የመመልመያ እድሜ ወደ 25 አመት ዝቅ ማለቱን ጨምሮ ዋናዋና ነጥቦችን አጠቃሎ አስቀምጧል።
የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ባለፈው ሳምንት በሰጡት የአመቱ ማጠቃለያ መግለጫ ዘለንስኪ የዩክሬን ጦር ግማሽ ሚሊዮን ወታደር ለመመልመል ምክረ ሀሳብ ማቅረቡን መናገራቸው ይታወሳል።
ዘለንስኪ ጉዳዩ ከባድ ስለሆነ እቅዱ ወደ ፖርላማ ከመላኩ በፊት መንግስት እና ጦሩ ሊመክርበት እንደሚገባም ገልጸው ነበር።
ዩክሬን ያላትን የጦር ብዛት ይፋ ባታደርግም፣ባለፉት አመታት አንድ ሚሊዮን የታጠቀ ጦር እንዳለት ገልጻለች።