የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት 22 ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ አሁንም እንደቀጠለ ነው
ሩሲያ 4 የዩክሬን ተዋጊ ጄቶችን መትታ መጣሏን ያስታወቀች ሲሆን፤ ዩክሬንም ሶስት የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖችን መትቼ ጥያለሁ ብላለች።
የሩሲያ እና የዩክሬን ወታደራዊ ባለስልጣናት ሁለቱም የጠላት አውሮፕላኖች እሁድ እለት 1,000 ኪሎ ሜትር በሚያካልለው ባለው የጦር ግንባር ክልል ውስጥ የጦር ጄቶችን መትተው መጣላቸውን አስታውቃል።
የዩክሬን አየር ሃይል አዛዥ ማይኮላ ኦሌሽቹክ እንዳሉት የዩክሬን ፀረ-አውሮፕላኖች በደቡባዊ ዩክሬን አዞቭ ባህር አካባቢ በምትገኘውና ሩሲያ በያዘችው ማሪፖል ከተማ አቅራቢያ የሩሲያ ሱ-34 ተዋጊ ቦምብ ጄቶችን መትቶ ጥለዋል።
ኦሌሽቹክ በቴሌግራም የመልእክት መላላኪያ ላይ ባሰረፉት ጽሁፍም የሩሲያ ተዋጊ ጄት ወደ ቦታው አልተመለሰም ከማለት በዘለለ ምንም ተጨማሪ ዝርዝር አልሰጡም።
የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ቀደም ብሎ ባወጣው መረጃ የሩሲያ የአየር መከላከያ ስርዓት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ አራት የዩክሬን ወታደራዊ አውሮፕላኖችን መመታቱን አስታውቋል።
የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የአየር መከላከያው በደቡብ ምስራቅ ዩክሬን በዛፖሪዝሂያ እና ዲኒፕሮፔትሮቭስክ ክልሎች ሶስት ሱ-27 ተዋጊ አውሮፕላኖች እና አንድ ሱ-24 ታክቲካል ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ተመትቶ ወድቋል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜለንስኪ ባሳለፍነው አርብ ሶስት የሩሲያ “ኤስዩ - 34” ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ተመትተው መውደቃቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል።
ሞስኮ እስካሁን ስለጦር አውሮፕላኖቿ መመታት አስተያየት አልሰጠችም።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት 22 ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ዩክሬን በርካታ የጦር አውሮፕላኖቿ ወድመውባታል።
በሞስኮ የተያዙ ግዛቶቿን ለማስመለስ ለምታደርገው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻም ከምዕራባውያን ተዋጊ ጄቶች እንዲቀርቡላት መመጻኗን ቀጥላለች።
ፕሬዝዳንት ዜለንስኪ በትናንት ምሽቱ መግለጫቸው አሜሪካ ሰራሹን “ኤፍ - 16” የጦር አውሮፕላን ከሆላንድ ለመቀበል ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ ጋር መነጋገራቸውን ገልጸዋል።
ከአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ልታገኘው የነበረው ከ100 ቢሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ ሳይጸድቅላት የቀረችው ዩክሬን ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ችግር እንደገጠማት ማሳወቋ የሚታወስ ነው።