ዘለንስኪ 2ኛ ዙር የኤፍ16 የጦር አውሮፕላኖችን መቀበላቸውን አስታወቁ
ዘለንስኪ ይህ አሜሪካ ሰራሽ የጦር አውሮፕላን የጦርነቱን ሁኔታ ሊቀይረው እንደሚችል የመጀመረያውን ኤፍ16 በተቀበሉበት ወቀት ተናግረው ነበር

ባለፈው ወር ምዕራባውያን ዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳይል ተጠቅማ ሩሲያ ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እንድትመታ መፍቃዳቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ጡዘት ላይ ደርሶ ነበር
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሁለተኛ ዙር የኤፍ16 የጦር አውሮፕላኖችን ከዴንማርክ መቀበላቸውን አስታውቀዋል።
"ሁለተኛ ዙር የኤፍ 16 የጦር ጀቶች ከዴንማርክ ዩክሬን ደርሰዋል።ዴንማርክ ህይወትን ለመታደግ ምሳሌ የሚሆን አመራር አላት" ብለዋል ዘለንስኪ።
ዘለንስኪ ይህ አሜሪካ ሰራሽ የጦር አውሮፕላን የጦርነቱን ሁኔታ ሊቀይረው እንደሚችል የመጀመረያውን ኤፍ16 በተቀበሉበት ወቀት ተናግረው ነበር።
ሁለት አመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ብቻ የቀሩት የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ባለፈው ወር ምዕራባውያን ዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳይል ተጠቅማ ሩሲያ ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እንድትመታ መፍቃዳቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ጡዘት ላይ ደርሶ ነበር።
ዩክሬን ወደ ሩሲያ ግዛት የአሜሪካ እና የእንግሊዝን የረጅም ርቀት ሚሳይሎች ተጠቅማ ጥቃት መፈጸሟ ሩሲያን በእጅጉ አስቆጥቷታል።
ሩሲያ ምላሽ የሰጠችው ፈጣን ኦሬሽኒክ የተባለ አዲስ ሚሳይል በማስወንጨፍ ነበር።
ሩሲያ አዲስ ሚሳይል ያስወነጨፈችው በጦርነቱ ዙሪያ ምዕራባውያን የሚያሳልፏቸው ሌሎች ውሳኔወችን ዝም ብለ እንዳማታልፍ ለማስጠንቀቅ ጭምር እንደነበር ተገልጿል። ፕሬዝደንት ፑቲን ሩሲያ በጦርነቱ አዲስ ሚሳይሎችን መጠቀሟን እንደምቀጥልበት መግለጻቸው ይታወሳል።
ዩክሬን በዚህ ሚሳይል የደረሰባትን የጉዳት መጠን ግልጽ ባታደርግም፣ ሚሳይሉ እጅግ ፈጣን እና አሁን ባላት የአየር መከላከያ ስርአት ማክሸፍ አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጻለች።
ሩሲያ እንደገለጸችው ሚሳይሉ የአሜሪካን ምዕራባዊ ክፍል እና አውሮፓው ውስጥ ያሉ የትኞቹንም ኢላማዎችን የመምታት አቅም እንዳለው አለው።
ሩሲያ እና ዩክሬን ያቀረባቸው የንግግር ቅድመ ሁኔታዎች የተራራቁ በመሆናቸው ምክንያት ጦርነቱን በድርድር ማስቅም አዳጋች ሆኗል።
ዩክሬን የምዕራባውያን ወታደራዊ እርዳታ የማይቋረጥባት ከሆነ የሩሲያን ኃይል ከግዛቷ እንደምታስወጣ ብትገልጽም፣ የሩሲያ ኃይሎች ቀስበቀስ በርካታ የምስራቅ እና ደቡብ ዩክሬን መንደሮችን መቆጣጠራቸውን ቀጥለዋል።