ሩሲያ የዩክሬንን መሰረተ ልማቶች በመምታት ዩክሬናዊያንን እና ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት ማሰቧን ኪቭ ገልጻለች
ዩክሬን የራሷን የሀይል ማመንጫ ልትመታ አቅዳለች መባሏን አስተባበለች።
የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ ሶስተኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።
የሩሲያ ስለላ ተቋማት ከሰሞኑ ዩክሬን የራሷን የሀይል ማመንጫዎችን በመምታት ሩሲያን የመክሰስ እቅድ እንዳላት ይፋ አድርገዋል።
ዩክሬን ሩሲያ በዩክሬናዊያን እና በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እንድትጠላ በማሰብ የራሷን መሰረተ ልማቶች ልትመታ እየተዘጋጀት ነው ብላለች።
የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ ሩሲያ የኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማቶችን ጨምሮ ዩክሬናዊያን ዜጎች የሚጠቀሙባቸውን ሌሎች መሰረተ ልማቶችን እያወደመች ነው ብሏል።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛራኮቫ የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ላወጣው መግለጫ በሰጡት ተጨማሪ ምላሽ ዩክሬን ሁለት የሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች ለመምታት እቅድ እንደያዘች ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
እንደ ቃል አቀባይዋ አስተያየት በድንፒሮ ወንዝ ላይ የተገነባው ኪቭ ሀይል ማመንጫ ግድብ እና ካኒዝ ግድብ መሆናቸው ተጠቅሷል።
ይሁንና ዩክሬን በሩሲያ የቀረበባትን ክስ ውድቅ ያደረገች ሲሆን የሞስኮ አስተያየት በዩክሬናዊያን ላይ እየፈጸመችው ያለው የጦር ወንጀል አንድ አካል መሆኑን አስታውቃለች።
ከአንድ ዓመት በፊት በሩሲያ ጦር ስር ያለው ካኮቭካ ግድብ ተመቶ በርካታ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኖ ነበር።
ለካኮቭካ ግድብ መመታት ዩክሬን ሩሲያን እንዲሁም አንዳቸው ሌላቸውን ሲከሱ ቆይተዋል።