ዩክሬን 69 ድሮኖችንና ሁሉት ሚሳይሎችን መትታ መጣሏን ገለጸች
ዩክሬን ከ73 ድሮኖች ውስጥ 69ኙን መትታ መጣሏን የዩክሬን አየር ኃይል በዛሬው ገልጿል።
ሁለት አመት ከሳባት ወራት ያስቆጠረው የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት አሁንም ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል
ዩክሬን 69 ድሮኖችንና ሁሉት ሚሳይሎችን መትታ መጣሏን ገለጸች።
ዩክሬን ሩሲያ ሌቱን ጥቃት በፈጸመችበት ወቅት ሁለት ባለስቲክ እና ሁለት ክሩዝ ሚሳይሎችን እንዲሁም ከ73 ድሮኖች ውስጥ 69ኙን መትታ መጣሏን የዩክሬን አየር ኃይል በዛሬው ገልጿል።
አየር ኃይሉ በቴሌግራም ገጹ ባወጣው መግለጫ የዩክሬን ኃይሎች ሁለት ክሩዝ ሚሳይሎችን መትተው ጥለዋል።
15 የሩሲያ ድሮኖች በኪቭ እና በኪቭ አቅራቢያ በአየር ኃይሉ ተመትተው መውደማቸውን በእዚያ ያለው ወታደራዊ አስተዳደር አስታውቋል። አስተዳደሩ አክሎ እንደገለጸው የድሮኖቹ ስብርባሪ በከተማዋ ክልል ውስጥ አርፏል።
"በዚህ ምክንያት መኖሪያ ባልሆኑ ህንጻዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት ሰለመኖሩ መረጃ የለንም" ብሏል አስተዳደሩ።
ሁለት አመት ከሳባት ወራት ያስቆጠረው የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት አሁንም ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል።
ዩክሬን ባለፈው ነሐሴ ወር በምዕራብ ሩሲያ ኩርስክ ግዛት ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት በምስራቅ ዩክሬን የተሰማራውን የሩሲያ ኃይል ለማዛባት አስባ የነበረ ቢሆንም የሆነው በተቃራኒው ነው።
የሩሲያ ኃይሎች ወደ ኋላ ሳያፈገፍጉ በግንባር ለተሰማራው የዩክሬን ኃይል ቁልፍ የሎጂስቲክስ ማስላለፊያ የሆነችውን የፖክርቭስክ ከተማ ለመያዝ መቃረብ ችላለች።
ሁለቱ ወገኞች የተራራቀ አቋም በመያዛቸው ምክንያት፣ጦርነቱን በድርድር ለማስቆሞ የተደረገው ጥረት አልተሳካም።
ዩክሬን፣ ሩሲያ ከግዛቷ ሙሉ በሙሉ ለቃ እንድትወጣ ስትጠይቅ፣ ሩሲያ ደግሞ ጦርነቱ እንዲቆም ዩክሬን በምዕራብ እና በደቡብ በኩል ካሉ ግዛቶች መውጣት አለባት የሚል አቋም ይዛለች።
ዩክሬን ምዕራባውያን ሀገራት የለገሷትን የረጅም ርቀት ሚሳይሎች ሩሲያ ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እንድትመታ እንደፈቅዱላት እየጠየቀች ነው። ፕሬዝደንት ፑቲን ምዕራባውያን ለዩክሬን ፍቃድ የሚሰጧት ከሆነ ከሩሲያ ጋር ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ ይገባሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።