ምስራቃዊቷ ዶኔትስክ ክልል ባለፈው በመስከረም ወር ወደ ሩሲያ ተጠቀለሉ ከተባሉ አራት ስፍራዎች ውስጥ አንዱ ነው
ምስራቃዊቷ ዶኔትስክ ክልል ባለፈው በመስከረም ወርምስራቃዊቷ ዶኔትስክ ክልል ባለፈው በመስከረም ወር ወደ ሩሲያ ተጠቀለሉ ከተባሉ አራት ስፍራዎች ውስጥ አንዱ ነው
ወደ ሩሲያ ተጠቀለሉ ከተባሉ አራት ስፍራዎች ውስጥ አንዱ ነው።
የዩክሬን ፕረዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ወታደሮቻቸው በምስራቃዊ ዩክሬን ዶኔትስክ በሚደረገው ጦርነት “አንድ ሴንቲ ሜትር” እንደማይሰጡ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳነረቱ ይህን ቢሉም በሩሲያ የተሾሙ ባለስልጣናት የዩክሬን ጦር ታንኮቹን ይዞ ወደ ደቡብ እየተመመ ነው ብለዋል።
የኢንዱስትሪ ክልል በሆነችው ዲኔትስክ ያለው ግጭት በባክሙት፣ ሶሌዳር እና አቪዲቪካ በተባሉ ከተሞች ዙሪያ ሲሆን፤ የሩሲያ ኃይሎች ባለፈው በየካቲት ወር መጨረሻ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ከፍተኛው ጦርነት ታይተዋል ነው የተባለው።
ዘሌንስኪ ማክሰኞ ምሽት በተንቀሳቃሽ ምስል ባስተላለፉት መልዕክት “የወራሪዎች እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ነው" ያሉ ሲሆን፤ በየቀኑ በርካታ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ናቸው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
"እነሱ እጅግ በጣም ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰባቸው ነው" በማለትም ስለ ጦርነቱ ወቅታዊ ሁኔታ ተናግረዋል። ሆኖም ትዕዛዙ ተመሳሳይ ነው፤ ይህም በዶኔትስክ ክልል አስተዳደራዊ ድንበር ላይ ለመሻገር ነው ብለዋል።
"አንድ ሴንቲ ሜትር መሬታችንን አንሰጥም" ሲሉም ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አቋማቸውን አሳውቀዋል።
ክልሉ በመስከረም ወር ውስጥ በሩሲያ ከእኔ ጋር ተጠቀለሉ ካለቻቸው አራት ስፍራዎች ውስጥ አንዱ ነው።
ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ በዩክሬን ጦር እና በሩሲያ ደጋፊ ኃይሎች መካከል ውጊያ ሲካሄድ ነበር።
በዚያሁ ዓመት ሩሲያ ክሬሚያን ወደ ከዩክሬን ቀንጥላ መቀላቀሏ ይታወሳል።