ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ፤ ዩክሬን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ትሰራለች አሉ
ዩክሬን ተጋላጭ ወደሆኑ የአፍሪካ ሀገራት የሰብዓዊ እህል ርዳታን በመላክ አህጉሪቱን ከዓላመዋ ጎን ለማሰለፍ እየታተረች ነው
ዘሌንሰኪ "በደርዘን ከሚቆጠሩ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት እያስተካከልን ነው" ብለዋል
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ኪቭ በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ እና በእስያ ያለውን "ትልቅ የኢኮኖሚ አቅም" እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ጥቅሞችን ለመጠቀም ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።
ሩሲያ በዬክሬን ላይ ጀመረችውን ወታደራዊ ዘመቻ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሲያወግዝ፤ የአፍሪካ ሀገራት አንድ አይነት አቋም መያዝ ተስኗቸው የተለያየ አቋም ሲያራምዱ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ይህ በተለይም እንደ ደቡብ አፍሪካ ያሉ አንዳንድ ሀገራት ከሩሲያ ጋር ያላቸውን የጠበቀ የንግድ እና የጸጥታ ግንኙነት አደጋ ላይ ላለማጣል እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡
ያም ሆኖ ዘሌንስኪ የኪቭ የዲፕሎማሲ ትኩረት ብዙም ተጽእኖ የለኝም ብላ ወደ ምታስበው ወደ ደቡብ የዓለም ክፍል አቅጣጫ መሆን እንዳለበት ትናንት በምሽት ለዲፕለማቶቻቸው ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት ተናግረዋል፡፡
በደቡብ የዓለም ክፍል "ትልቅ የኢኮኖሚ አቅም እና ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ መንገዶች አሉ"ም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
በተጨማሪም ዩክሬን ከባህላዊ አጋሮቿ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር እንደምትፈልግ መግለጻቸው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ቀደም ሲል ለዲፕሎማቶች በሰጡት አስተያየት፤ ከአፍሪካ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማስፋት የተደረጉ ሙከራዎችን ለይቷል።
ቢዘህም ዩክሬን በተጋላጭ ሀገራት ውስጥ ያለውን ረሃብ ለመቅረፍ የሰብዓዊ እህል ርዳታን በመላክ የአፍሪካ ሀገራትን ከዓላማዋ ጎን ለማሰለፍ ስትሞክር ቆይታለች።
ሩሲያ፤ ዬክሬን በጥቁር ባህር በኩል ወደ ውጭ የምትልካቸው የግብርና ምርቶች ማገዷን ተከትሎ በዚህ አመት ዓለም አቀፍ የእህል እና የማዳበሪያ እጥረት አስከትሎ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
በዚህም በተባበሩት መንግስታት አደራዳሪነት በሐምሌ ወር ስምምነት ላይ ተደርሶ በከፊል መለቀቅ እስከጀመረበት ድረስ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን አደጋ እንዲወድቁ ምክንያት ሆነ ነበር፡፡
በተፈጠረው ነገር እጅጉን ማዘናቸው የገለጹት ፕሬዝዳንት ዘሌንሰኪ አሁን ላይ "በደርዘን ከሚቆጠሩ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት እያስተካከልን ነው" እናም በሚቀጥለው ዓመት ይህንን ማጠናከር አለብን ሲሉም ለዲፕሎማቶቻቸው ተናግረዋል።
ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጎልበት ዩክሬን በአህጉሪቱ ውስጥ ባሉ በርካታ ማዕከሎች ውስጥ የንግድ ተወካይ ጽ / ቤቶችን ማቋቋም እንደምትፈልግም ጭምር አስታውቀዋል፡፡
እነዚያ አዳዲስ ኤምባሲዎች ወይም የንግድ ቢሮዎች የት እንደሚገኙ ግልጽ ያላደረጉት ዘሌንሰኪ፤ ዩክሬን በአህጉሪቱ 30 ሀገራት እንድትወከል እናደርጋለን ሲሉም አክለዋል፡፡