70 ሽህ የሚጠጉ ነዋሪዎች የነበሯት ባክሙት ከተማ ላለፉት ዘጠኝ ወራት የሩሲያ ዋነኛ ኢላማ ሆናለች
ሞስኮ አይኗን በጣለችባት በባክሙት አዲስ ግፊት ስትጀምር፤ ዩክሬን ከተማዋን ለቃ እየወጣች ነው ተብሏል።
የዩክሬን ወታደሮች በሩሲያ አዲስ ጥቃት ከአንዳንድ የባክሙት አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ መገደዳቸውን ብሪታንያ አስታውቃለች።
የዩክሬን ባለስልጣናት ሩሲያ ለዘጠኝ ወራት ያህል ለመያዝ እየጣረች ባለችው ባክሙት ላይ ከፍተኛ ግፊት ለማድረግ በግንባሩ ላይ ከሌሎች አካባቢዎች ወታደሮቿን እያሰፈረች ነው ብለዋል።
በባክሙት አካባቢ የዩክሬን ጦር ሰራዊት ወታደሮች እየተኮሱ ነበር ያለው ሮይተርስ በዘገባዉ፤ ሩሲያ የእግረኛ ወታደሮቿን በጅምላ ጨምራለች ብሏል።
የዩክሬን ምክትል የመከላከያ ሚንስትር ሃና ማሊያር የሩስያ አዛዦች ወታደሮችን ከሌሎች አካባቢዎች ወደ ባክሙት አዛውረዋል ብለዋል።
"ጠላት በጣም ከፍተኛ መጠን ያለው የመድፍና የአየር ጥቃት እየፈጸመ ነው" ብለዋል።
ከጦርነቱ በፊት ወደ 70 ሽህ የሚጠጉ ነዋሪዎች የነበሯት ባክሙት፤ የሩሲያ ዋነኛ ኢላማ ሆናለች።