የሩሲያው ተዋጊ ዋግነር ግሩፕ አብዛኛውን የባክሙት ክፍል መቆጣጠሩን ገለጸ
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ከአንድ አመት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን እስካሁን እንደቀጠለ ነው
የዩክሬን ጦር ቃል አቀባይ ግን በባክሙት ያለው ሁኔታ በቁጥጥር ስር መሆኑን እና ወታደሮቹ እንዲከበቡ እንደማይፈቅዱ እየገለጹ ይገኛሉ
የሩሲያ ዋግነር ቅጥረኛ ቡድን መሪ ማክሰኞ እንዳስታወቁት ጦርነቱ ከባድ እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ከተካሄደ በኋላ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዩክሬኗን ባክሙት ከተማን ተቆጣጥሯል።
የዩክሬን ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ስጉዳዩ በቀጥታ ባይናገሩም ኃይሎቻቸው አሁንም ከተማዋን በመከላከል ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የዋግነር ተዋጊዎች ሩሲያ ባክሙትን ለመያዝ ለወራት የፈጀውን ጥረት መርተዋል።
በሁለቱም ወገኖች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው የምሽግ ጦርነት እና የማያቋርጥ የመድፍ ጦርነቶች ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ጋር እንዲመሳሰል አድርጎታል።
የዋግነር ኃላፊ ዬቭጄኒ ፕሪጎዝሂን እንዳሉት በምስራቅ ሩሲያ ለሚደረገው ግስጋሴ ትልቅ ሚና የተጫወቱት ሀይሎቹ ባክሙትን ከበው እየገፉ ነው።
በሩሲያ ወታደራዊ ጦማሪ በተለጠፈው ቪዲዮ ላይ "በባክሙት ትልቁ ክፍል ከ 80 በመቶ በላይ አሁን በእኛ ቁጥጥር ስር ነው። በአጠቃላይ የአስተዳደር ማእከል፣ፋብሪካዎች፣መጋዘኖች እና የከተማው አስተዳደር" በቁጥጥር ስር ናቸው ብለዋል።
ባለፈው መስከረም ወር በሞስኮ ቁጥጥር ስር ከዋሉት አራት አካባቢዎች አንዱ የሆነው የዶኔትስክ ክልል ርእሰ መስተዳድር የሩስያ ጦር የዩክሬንን ተከላካዮች ወደ አንድ ጥግ እንደደገፋቸው ተናግሯል።
ዴኒስ ፑሺሊን ለመንግስት ቴሌቪዥን እንደተናገረው የሩሲያ የዜና ኤጀንሲዎች "ክፍላቸው በተቆፈረባቸው ምዕራባዊ አካባቢዎች ወደ ፊት ከመቅረብ እና እራሳቸውን ከመስጠት ውጭ ሌላ አማራጭ የላቸውም" ብለዋል።
የዩክሬን ጦር ቃል አቀባይ ግን በባክሙት ያለው ሁኔታ በቁጥጥር ስር መሆኑን እና ወታደሮቹ እንዲከበቡ እንደማይፈቅዱ እየገለጹ ይገኛሉ።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ከአንድ አመት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን እስካሁን እንደቀጠለ ነው
አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት ዩክሬንን መደገፋቸውን ቀጥለዋል።