የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት የሀገር ክህደት ፈጽመዋል ያሏቸውን ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናት አባረሩ
ዘለንስኪ የደህንነት ሃላፊው ባካኖቭን የተመለከቱ "በቂ ማስረጃዎች" ሰብስባናል ብለዋል
ዘለንስኪ አሁን በክህደት የሚከስዋቸው ሰዎች ቀድሞም ቢሆን በወዳጅነት እንጅ በበብቃት የመጡ እንዳልሆነ ይነገራል
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የሀገር ክህደት ፈጽመዋል ያሏቸውን ሁለት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ከሃላፊነት አባረሩ፡፡
ፕሬዝዳንቱ ከሃላፊነት ያባረርዋቸው ባለስልጣናት የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኢሪና ቬኔዲክቶቫ እና የዩክሬን የሀገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊ ኢቫን ባካኖቭ ናቸው።
ትናንት ሌሊት ያልተጠበቀ ንግግር ያደረጉት ዘለንስኪ በሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት እና የአቃቤ ህግ ቢሮ ከሩሲያ ጋር በማበር ከዩክሬን ጥቅም ተቃራኒ የቆሙ 60 ባለስልጣናት እንዳሉና ለዚህም 651 የሀገር ክህደት እና የትብብር ክሶች በህግ አስከባሪ ባለስልጣናት ላይ መከፈታቸው ላይ ተናግረዋል፡፡
"እንዲህ ያሉት የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንነት መሰረት የሚጥሱ ወንጀሎች... በሌሎች የተለያየ የሃላፊነት ቦታ ላይ ያሉ አካላት ጥያቄዎችን ፈጥረዋል" ያሉት ፕሬዝዳንቱ "እነዚህ ጥያቄዎች እያንዳንዳቸው ትክክለኛ መልስ ያገኛሉ” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
ዘለንስኪ የደህንነት ሃላፊው ባካኖቭን የተመለከቱ "በቂ ማስረጃዎች" ሰብስባናል ማለታቸውም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
“እነዚህ ሁሉም የወንጀል ተግባራቶቹ በሰነድ የተቀመጡ ናቸው” ሲሉም አክለዋል።
በጦርነት ጊዜ በመሲጠረዋቸው መግለጫዎች የዓለም አቀፉን ማህበረስብ ትኩረት በመሳብ የሚታወቁት ፤ ሩሲያ በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ ከመጀመሯ በፊት ልምድ የሌላቸውን የውጭ ሰዎች፣ ጓደኞቻቸውን ጨምሮ፣ ለሚመሩት የሙያ መስክ ቅረበት የሌላቸው ሰዎች በመሾም ሲተቹ የነበሩ መሪ ናቸው፡፡
ለዚህም የልጅነት ጓደኛቸውና እንደሆኑና ዘለንስኪን የሚዲያ ንግድ በቴሌቪዥን ህይወቱ እንደሚመሩ ትልቅ ውለታ እንደዋሉላቸው የሚነገርላቸው ባካኖቭ የደህንነት ሃለፊ አድረገው መሾማቸው እንደ አብነት ይነሳል፡፡
ባለፈው ሳምንት በሄግ በዩክሬን ተፈጽመዋል የተባሉት የሩስያ የጦር ወንጀሎችን ለመክሰስ በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ላይ ሲካፈሉ የቆዩ እንስቷ ቬኔዲክቶቫም ቢሆኑ ዘለንስኪ ወደ ፖለቲካ ከገቡ በኋላ በፍትህ ማሻሻያ ጉዳዮች ዙሪያ ሲያማክሩ የቆዩ የቅርብ ወዳጃቸው ናቸው፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ሩሲያ የዩክሬን ሰፊ መሬት ብትቆጣጠርም የምዕራባውያን የጦር መሳሪያዎች በዬክሬን ምድር መድረስ በጦር ሜዳ ውጤት ማሳየት ጀምሯል።
የዩክሬን ጥቃቶች በሩስያ የአቅርቦት መስመሮች ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሱ ሲሆን የሩሲያን የማጥቃት አቅም በእጅጉ እንደቀነሰም የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሌላ በኩል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ፤ ወታደራዊ ክፍሎች በሩሲያ በተያዙ አካባቢዎች ላይ የዩክሬን ጥቃቶችን ለመከላከል ዘመቻውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ቅዳሜ ዕለት ማዘዛቸው የሚታወስ ነው፡፡