“ዩክሬናውያን አትሽሹ፣ ተስፋ አትቁረጡ፤ መዋጋታችሁን አታቁሙ”- ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ
የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ግዙፉን የኑክሊየር ጣቢያ ጨምሮ በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥረዋል
ዩክሬን ምእራባውያን ሀገራት በዩክሬን ከበረራ ነጻ ቀጣና እንዲያውጁ ብትጠይቅም፤ ከሩሲያ ጋር በቀጥታ ያጋጨናል በሚል ጥያቄዋን አልተቀበሏትም
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በቴሌቪዥን የዩክሬናውያን ቆራጥነት እና አንድነት የሩሲያን ኃይሎች እንደሚያባርር ለዩክሬናውያን ባስተላለፈው የቴሌቪዥን መግለጫ አስታውቋል፡፡
“የኛ ህዝብ፣የኛ ዩክሬናውያን አትሽሹ፡፡ ተስፋ አትቁረጡ፡፡ መከላከላችሁን አታቁሙ፡፡ ወራሪዎች ወደ ቤታችሁ ሂዱ እያሉ እየጮሁ ነው” ብሏል ዘለንስኪ፡፡
- አሜሪካ ከሩሲያ እንዲዋጋ ወደ ዩክሬን የምትልከው ጦር እንደማይኖር አስታወቀች
- በዩክሬን የሚገኘው የአውሮፓ ትልቁ የኒዩክለር ጣቢያ በሩሲያ ቁጥጥር ስር ዋለ
- የአፍሪካ ሀገራት ሩሲያን እንዲያወግዙ አሜሪካ ጠየቀች
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በተገንጣዮች ቁጥጥር ስር የሚኖሩ ሰዎች ዩክሬን ትጠላችኋለች እናም ማጥፋት ትፈልጋለች እያለ የሚነግራቸውን “የሩሲያን ቴሌቪዥን ውሸት” እንዳይቀበሉ ጠይቋል፡፡
“በጊዜያዊነት በተወረሩ አካባቢ ያሉ ሁሉም ህዝብ እንጠይቃለን፡፡ የሚሰሙንን ሁሉ፡፡ የማስታወስ አቅማቸው በፕሮፓጋንዳ ያልጠፋባቸውን ሰዎች፡፡ አይናቸው በፍርሃት ያልተከደነባቸውን፡፡ ነፍሳቸው በትችት ያልተጎዳባቸውን“ሲሉ ዘለንስኪ ተናግረዋል፡፡
በምእራባውያን የምትደገፈው ዩክሬን፣ ምእራባውያን በዩክሬን ከበረራ ነጻ ቀጣና እንዲያውጁ ብትጠይቅም፤ ምእራባውያን ርምጃው ቢወሰድ ከሩሲያ ጋር በቀጥታ ስለሚያጋጭ አናውጅም ብለዋል፡፡
የምእራባውያን ወታደራዊ ጥምረት በሆነው የኔቶ ድክመት ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ ሲሉ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በትናንትናው እለት ተናግረዋል፡፡
ምእራባውያን ይህን ባለማድረጋቸው ዩክሬን ብቻዋን እየዋጋች ነው ሲሉ ዘለንስኪ ተደምጠዋል፡፡
ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ “በዩክሬን የተጀመረው ወታደራዊ ተልዕኮ” ሀገራቸው ባቀደችው መልኩ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የሩሲያ ጦር እስካሁን ባካሄደው “ዘመቻ” በደቡብ ዩክሬን የምትገኝው ኬርሶን ከተማ ጨምሮ ሌሎች ቦታዎችንና ከተሞችን መቆጣጠር ችሏል፡፡ የሩሲያ ወታራዊ ዘመቻ በምዕራባውያን ዘንድ ያልተወደደ በመሆኑ በርካታ የኢኮኖሚ ማዕቀቦች ጎርፍ እየወረደባት ነው፡፡ ምዕራባውያን የኢኮኖሚ ማእቀብ ከመጣል በተጨማሪ የአየር ክልላቸውን ለሩሲያ ዝግ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯን የሚያወግዘዉን የዉሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት የከፈተችው፣የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ የሶቬት ህብረት ሀገራት እተሰፋፋ ነው፤ይህም ለደህንነቷ አስጊ እንደሚሆን በመግለጽ ነበር።የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እደቀጠለ ቢሆንም ሀገራቱ ችግሩን ለመፍታት ሁለተኛ ውይይታቸውን ጀምረዋል።