የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ የውሳኔ ሃሳብን ኤርትራ ስትቃወም፤ 16 የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ ድምጸ ተአቅቦ ማድረጋቸው ይታወሳል
ሩሲያ በዩክሬን እያደረገች ያለውን “ወታደራዊ ተልዕኮ” የአፍሪካ ሀገራት እንዲየወግዙ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጠየቀ፡፡
ምንም እንኳን የአፍሪካ ሀገራት የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን የውሳኔ ሃሳብ ቢደግፉም አሁንም ሌሎች ሀገራት ሩሲያን ማውገዝ እንዳለባቸው ዋሸንግተን ጠይቃለች። የፖለቲካ አዋቂዎች የአፍሪካ ሀገራት ስለጦርነቱ ጥቂት ነገር ብቻ እያሉ መሆኑን ገልጸዋል።
በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ሞሊ ፊ ዩክሬናውያን የአፍሪካን ድጋፍ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።
ዋሸንግተን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ የአፍሪካ ድምጽ አስፈላጊ መሆኑን እንደምታምን የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል።
ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አሁን ላይ በአንድ ላይ ሆኖ ድምጹን እያሰማ መሆኑን የገለጸችው አሜሪካ፤ ይህም ሉዓላዊነትን፣ ግዛታዊ አንድነትን፣ ግጭቶችን በሰላም መፍታትን እና የንጹሃንን ህይወት መታደግን የሚጠይቅ እንደሆነ አስታውቃለች፡፡
ባለፈው ማክሰኞ የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ የውሳኔ ሃሳብ ላይ 141 ሀገራት ሲደግፊት ከአፍሪካ ኤርትራ ብቻ ተቃውማው የነበረ ሲሆን 16 የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ ድምጸ ተአቅቦ አድርገው ነበር።
አንድ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር አፍሪካ ብዙ የሀገር ቤት ጣጣ ስላለባት በውጭ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ እንደማትችል ገልጸዋል።
ፕሮፌሰሩ፤ አፍሪካውያን “የራሳችን ብዙ ችግሮች አሉብን፤ በመሆኑም በውጭ ጉዳዮች ላይ እንዲንገባ አይመከርም” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
ምንም እንኳን ካሳጅ አፑሊ የተባሉት እኒህ ፕሮፌሰር አፍሪካ በውጭ ጉዳዮች ላይ አትሳተፍም ቢሉም ኬንያና ደቡብ አፍሪካን የመሳሰሉ ሀገራት በዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት ላይ ቀድመው አስተያየቶችን ሲሰጡ ነበር።
ሌላው የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ ደግሞ አፍሪካ በዚህ ጦርነት ከየትኛውም ወገን እንደማትሆን ገልጾ ይሁንና ሀገራት በዓለም አቀፍ ሕግ ያላቸው መብት እንዲከበር ማድረግ አለባት ብለዋል።