ተመድ የእርዳታ ስርጭት ያቋረጠው እስራኤል የስርጭት ማዕከሉ ከሚገኝበት ዴር አል በላህ ነዋራዎች ለቀው እንዲወጡ አዲስ ትዕዛዝ ካስተላለፈች በኋላ ነው
እስራኤል አዲስ የለቃችሁ ውጥ ትዕዛዝ ማስተላለፏን ተከትሎ ተመድ በጋዛ የሚያደርገውን የእርዳታ ስርጭት ማቋረጡ ተገልጿል።
ተመድ ሲያካሂድ የነበረውን የእርዳታ ስርጭት ያቆመው እስራኤል የስርጭት ማዕከሉ ከሚገኝበት ዴር አል በላህ ነዋራዎች ለቀው እንዲወጡ አዲስ ትዕዛዝ ካስተላለፈች በኋላ ነው።
ይህ ትዕዛዝ የመጣው ተመድ በቀጣይ ቅዳሜ በጋዛ የሚገኙ ከ640ሺ በላይ ህጻናትን ለመከተብ እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት ነው። የአለም ጤና ድርድት በጋዛ በ25 አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የ10 አመት ህጻን በታይፕ 2 ፖሊዮቫይረስ ተጠቅቶ መንቀሳቀስ የማይችልበት ደረጃ መድረሱን ወይም ፓራላይዝድ መሆኑን ገልጿል።
ተመድ ዋና ማዕከሉን እና አብዛኛዎቹን ሰራተኞቹን ወደ ዴየር አልባላህ ያዛወረው፣ እስራኤል ከወራት በፊት ከደቡብዊ ጋዛ ራፋ እንዲለቁ ካደረገቻቸው በኋላ ነው።
"አሁን ወዴት ነው የምንሄደው?" ያሉት የተመድ ባለስልጣን አክለው እንደገለጹት የተመድ ሰራተኞች በፍጥረት ቦታ መቀየር አለባቸው።
አንድ ከፍተኛ የተመድ ባለስልጣን እንደማሉት ከሆነ ሰራተኞቹ አዲስ መንገድ ፈልገው ስራቸውን እንዲቀጥሉ ተነግሯቸዋል ብለዋል። ባለስልጣኑ እንዳሉት የተመድ ስራ በይፋ አልተቋረጠም።
"ህዝቡ ስለሚፈልገን ጋዛን አንለቅም" ብለዋል ባለስልጣኑ። "የህዝቡን ፍላጎት እና የተመድ የሰራተኞቹን ደህንነት ለማመዛዘን እየሞከርን ነው።"
የተመድ የፍልስጤማውያን ስደተኞች ኤጀንሲ(ዩኤንአርደብሊውኤ) ከፍተኛ የፊልድ ዳይሬክተር ሳም ሮዝ የጤና እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማቅረብ ጥረት ቢኖርም ችግር እንዳጋጠማቸው ገልጸዋል።
"አሁን በትንሽ የጋዛ አካባቢ ላይ እንድንወሰን ተገደናል" ብለዋል።
ለሰብአዊ አገልግሎት በእስራኤል የተፈቀደው ከጠቅላላው የጋዛ ክፍል 11 በመቶ መሆኑን እና አሁን ላይ እየቀነሰ መሄዱን ተናግረዋል ዳይሬክተሩ።
https://am.al-ain.com/article/un-aid-operation-gaza-haltሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት ከ40ሺ በላይ ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል።